የዘር ሐረግ ምርመራ /DNA/ የሚታወሰን የቤተሰብ
ዝምድናን ለማረጋገጥ ሲከወን ነው፡፡ የአባት እና ልጅነት ክርክሮችን ለመፍታት ሁነኛ መላ አድርገነው ሰንብተናል፡፡ የዘር ሐረግ
ምርመራ በአብላጫ ተመራማሪዎች ይሁንታን ተችሮታል፡፡ በበርካታ ሐገሮችም ተቀባይነት አግኝቶ እየተሰራበት ይገኛል፡፡ በአሜሪካ የዜግነት
እና የወላጆች መረጃ 99.99 በመቶ ተቀባይነት አለው፡፡ (100% ላለማለት ይመስላል)
ዲ.ኤን.ኤ
ምንድነው?
ዲ.ኤን.ኤ
(Deoxyribonucleic Acid) በጣም ጥልቅ “ሞልዩኪል” ሆኖ ህይወት
ያላቸውን ማናቸውንም ፍጡራን፣ አትክልት፣
እንስሳት፣ ባክቴሪያ ወዘተ
የዘር-ቀመር (Genetic code) ያዘለ ነው።
የአንድ ፍጡር ዲ.ኤን.ኤ
በዚያ ፍጡር ማናቸውም ህዋስ (ሴል) ውስጥ
ይገኛል። እያንዳንዱ በምድር
ላይ ያለ ፍጡር የራሱ የሆነ ልዩ ባህርይ እንዲኖረውም ያደርጋል። ይህ የሚሆነው ማንኛውም ፍጡር አካሉን የሚገነባባቸው “የፕሮቲን ሞለኪሎችን” አመራረት የሚመራው ዲ.ኤን.ኤ
በመሆኑ ነው፡፡
የአንድ ህዋስ “ፕሮቲን”
የዚያን ህዋስ ተግባር
ይወስናል። ዲ.ኤን.ኤ
ከወላጅ ወደ ልጅ
ይተላለፋል፡፡ ስለሆነም ወላጆችና
ልጆች ተቀራራቢ ባህርይ እና መልክ እንዲኖራቸው
ያደርጋል። አንድ ዓይነት
የማይሆኑበት ምክንያት ልጆች
ከሁለቱ ወላጆች ድብልቅ
ዲ.ኤን.ኤ ስለሚወርሱ
ነው።