Saturday, March 10, 2018

የጥያቄዎቹ የአመላለስ መንገድ ይታረም!


በአንድ ወቅት ማህተመ ጋንዲ ‹‹የሐሳብ መለያየት ጠላትነት አይደለም፡፡ እንደዚያ ቢሆን ኖሮ ዋነኛ ጠላቴ ሚስቴ ትሆን ነበር፡፡›› በማለት ተናግረዋል፡፡ በሐሳብ መለያየት አለመዋደድ አይደለም፡፡ በአንድ ርእሰ ጉዳይ የተለያየ አቋም መያዝ የጠላትነት ምልክት አይደለም፡፡ አንዱ የስልጣኔ መለኪያ የማይጥምህን ሐሳብ ታግሶ ማድመጥ መቻል ነው፡፡
 
ያለፉትን ዓመታት የሐገራችንን ክራሞት ስንታዘብ የሥህተቱ መጀመሪያ ልዩነትን መጥላት ነው፡፡ ተቃውሞን አለመሻት ነው፡፡ በዓለም ዙሪያ የሥልጣን መንበሩ ላይ በንግስና ካሉት መኻል መቶ በመቶ ህዝቡን ያስደሰተ መንግስት የለም፡፡ አልነበረም፡፡ ወደፊትም አይኖርም፡፡ ሥርአቱን የማይደግፍ ሊኖር ይችላል፡፡ እንኳን መጥፎ የሚባለውን ድርጊት ጥሩ ነገሮችም የማይዋጡለት ሊኖር ይችላል፡፡ ነገር ግን የአጠቃላይ ስዕሉ አንድ ቀለም ነውና አይጣልም፡፡ የግዙፉ ምስል ትንሽ ክፍል ነውና ከጨዋታ ሜዳው አይባረርም፡፡

የኢትዮጵያዊያን የዘር ግንድ ምርመራና ውጤቱ


የዘር ሐረግ ምርመራ /DNA/ የሚታወሰን የቤተሰብ ዝምድናን ለማረጋገጥ ሲከወን ነው፡፡ የአባት እና ልጅነት ክርክሮችን ለመፍታት ሁነኛ መላ አድርገነው ሰንብተናል፡፡ የዘር ሐረግ ምርመራ በአብላጫ ተመራማሪዎች ይሁንታን ተችሮታል፡፡ በበርካታ ሐገሮችም ተቀባይነት አግኝቶ እየተሰራበት ይገኛል፡፡ በአሜሪካ የዜግነት እና የወላጆች መረጃ 99.99 በመቶ ተቀባይነት አለው፡፡ (100% ላለማለት ይመስላል)
ዲ.ኤን.ኤ ምንድነው?
ዲ.ኤን.ኤ (Deoxyribonucleic Acid) በጣም ጥልቅሞልዩኪል” ሆኖ ህይወት ያላቸውን ማናቸውንም ፍጡራን፣ አትክልት እንስሳትባክቴሪያ ወዘተ የዘር-ቀመር (Genetic code) ያዘለ ነው። የአንድ ፍጡር .ኤን. በዚያ ፍጡር ማናቸውም ህዋስ (ሴል) ውስጥ ይገኛል። እያንዳንዱ በምድር ላይ ያለ ፍጡር የራሱ የሆነ ልዩ ባህርይ እንዲኖረውም ያደርጋል። ይህ የሚሆነው ማንኛውም ፍጡር አካሉን የሚገነባባቸው “የፕሮቲን ሞለኪሎችን” አመራረት የሚመራው ዲ.ኤን.ኤ በመሆኑ ነው፡፡
የአንድ ህዋስፕሮቲን” የዚያን ህዋስ ተግባር ይወስናል። .ኤን.ኤ ከወላጅ ወደ ልጅ ይተላለፋል፡፡ ስለሆነም ወላጆችና ልጆች ተቀራራቢ ባህርይ እና መልክ እንዲኖራቸው ያደርጋል። አንድ ዓይነት የማይሆኑበት ምክንያት ልጆች ከሁለቱ ወላጆች ድብልቅ ዲ.ኤን. ስለሚወርሱ ነው።

የአእምሮ ንብረት እና ተዛማጅ መብቶች



ሐገራችን አባል ካልሆነችባቸው (ካልፈረመቻቸው)፣ ዓለምአቀፍ አስገዳጅ ስምምነቶች አንዱ የቅጂና ተዛማጅ መብት ነው፡፡ ይህም ለዜጎች ከሚሰጠው ጥቅም በላይ፣ ጉዳቱ የሚያመዝን በመሆኑ የተደረገ ነው፡፡ እየተጠቀምንበት ባለው ኮምፒውተር ላይ ያሉት እያንዳንዳቸው ‹ሶፍትዌሮች›፤ የእጅ ተንቀወሳቃሽ ስልካችን ላይ የሚገኙት እያንዳንዳቸው መተግበሪያዎች ‹አፕሊኬሽኖች›፤ በቅናሽ የዋጋ ተመን እጆቻችን የገቡት በዚያ ምክንያት ነው፡፡ በየኮሌጅና ዩኒቨርሲቲዎች በቅጂ (በኮፒ) እየተባዙ ተጠርዘው የተማርንባቸው መጻሕፍት፣ ከዋናው መሸጫቸው ባነሰ ዋጋ የምንገዛቸው በዚያ ሰበብ ነው፡፡ 

ስህተት በስህተት አይታረምም!


ሐገራችን ያለችበት ሁኔታ አሳሳቢ ነው፡፡ ቀድመን በትንሽ በትንሹ እያጠራቀምን ያመጣናቸው ችግሮች ተራራ አክለው ተጋፍጠውናል፡፡ ሁላችንም የየድርሻችንን በቀላሉ ያዋጣንበት የስህተት ማጥ በቀላሉ ልንቋቋመው እንዳንችል ሆኗል፡፡ ዓለማቀፍ ሚድያዎች ሳይቀሩ መስቀለኛ መንገድ ላይ መቆማችንን እየዘገቡ ይገኛሉ፡፡ ሁኔታችንን ታዝቦ፤ ድርጊታችንን ተመልክቶ፤ ነጋችንን ተንብዮ፤ አለመፍራት አይቻልም፡፡ 

Monday, December 11, 2017

ያልተገባ አድናቆት የወለዳቸው የጥበብ ሥራዎች

ለሰሩ ሰዎች፤ ልከኛ በሆነ መንገድ ተጉዘው የራሳቸውን በጎ አሻራ ላኖሩ ጥበበኞች፤ ምስጋናን መቸር ተገቢ ነው፡፡ ለላቀው ጥበባቸው አድናቆት እና ሽልማት ማበርከት እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ የዚህ ክዋኔ ግብረመልስ ከዋነኞቹ የአሁን ጥበበኞች በላይ ለከርሞ ተተኪዎች የጎላ ጠቀሜታ አለው፡፡ በጠንካራ ሥራዎቹ ሰበብ እውቅና የተሰጠው፤ በላቀ አበርክቶው ምክንያትነት ምስጉን ለመባል የበቃ፤ . . . የጥበብ ዋርካ ሲበረክት አርዓያ የሚያደርጉት የነገ ፍሬዎች ቁጥር እንዲያሻቅብ ያግዛል፡፡ ሁኔታው ለጠጥ ተደርጎ ሲታሰብ እንደ ሐገር እየተተካካን ሩቅ እንድንጓዝ የሚያስችለንን ነዳጅ የሚሞላልን ግብአት ነው፡፡

Saturday, November 4, 2017

ኢትዮጵያዊነትን የምታስተጋባ አርቲስት - እጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ)

ሙዚቃ የዘመን ሥራ ነው፡፡ ዘመኑን ይመስላል፡፡ በድምፆቹ ዘመን
ን ያሳያል፡፡ በግጥም ሐሳቦቹ ጊዜ የወለደውን እሳቦት ይናገራል፡፡ የ1960ዎቹን የኢትዮጵያን ሙዚቃዎች የምንለየው በቅንብር መንገዳቸው (Orchestration) ነው፡፡ የ1970ዎቹንም እንዲሁ ከ60ዎቹ ከወሰዷቸው በጎ እሴቶች ጋር የራሳቸውን ደምረው (የተዉአቸው/ያልወሰዷቸው ታሳቢ ተደርገው) የበርካታ መሳሪያዎችን ድምፅ ማስደመጥ የሚያስችል የሙሉ ባንድ(Natural) የቅንብር ዘዬን በመከተላቸው ነው፡፡ እነ ሮሐ  እነ ዋልያስ ባንዶችን መጥቀስ ይቻላል፡፡

Wednesday, October 11, 2017

ከሳሽ የለም እንጂ፤ ተከሳሽስ ሞልቶ ነበር

ቀደም ባለው ጊዜ በሐገራችን የሚሰራጩ የሬዲዮ እና የቴሌቪዥን ጣቢያዎቻችን ቁጥር አነስተኛ ነበር፡፡ 16ዓመት በፊት FM 97.1 ሳይጀመር፤ ጣቢያዎቹ የሚያስተላልፏቸው ፕሮግራሞች በህብረተሰቡ ዘንድ ያላቸው ተቀባይነት ደግሞ ከፍተኛ ነበር፡፡ የዕጅ ሰዓትን ለመሙላት ሳይቀር ማንጸሪያ እና መከራከሪያ ነጥቡ ከራዲዩ እኩል መሆኑ ነበር፡፡ አሁን በርከት ያሉ የራዲዮ ጣቢያዎች ባለቤት ነን፡፡ /የግልም የመንግስትም/ ለኢትዩጵያዊ ታዳሚ እንዲደርሱ ታልመው የሚሰናዱ የሳተላይትና የሀገር ውስጥ ቴሌቪዥን ጣቢያዎች ቁጥርም በማሻቀብ ላይ ነው፡፡ የተአማኒነቱ ጉዳይ ግን ቀስ በቀስ እየተሸረሸረ መጥቷል፡፡ ዛሬ ዛሬ በራዲዮ ድምጽን ማሰማት የጥቂት ደቂቃዎች ሙከራ ውጤት ነው፡፡ እንደቀደመው ዘመን ከፍ ያለ ትጋት አይጠይቅም፡፡

Wednesday, September 6, 2017

ከ ‹ፍቅር እስከመቃብር› የተነሱ ሌሎች ኪነ-ጥበባዊ ሥራዎች



በዘመን እና ጥበብ መጽሔታችን የሰኔ ወር እትም ‹ተወራራሽ የኪነ-ጥበብ ሥራዎች› በሚል ርዕስ ሥር መጨዋወታችን ይታወሳል፡፡ መነሻቸውን አስቀድሞ ለታዳሚ በደረሰ የኪነ- ጥበብ ውጤት ላይ ያደረጉ ሥራዎችን በወፍ በረር ቃኝተናል፡፡ ያነሱትን የጥበብ ውጤት፤ ቀድሞ የነበረውን እንደነበረ በሌላ የጥበብ ዘውግ፤ ወይም ነባሩን ይዘው በሌላ ዓዲስ የሀሳብ መንገድ የተገለፁትን ዘርዝረናል፡፡ በእግረመንገድ ያስተዋልነውን፣ በትውስታ ማህደራችን ቀድመው የተከሰቱልንን ብቻ አነሳስተናል፡፡

ወጋችንን ስናሳርግ ‹ፍቅር እስከ መቃብር› የተሰኘው ረዥም ልብወለድ ላይ ተመስርተው የተሠሩትን ለማነሳሳት ቃል ገብተን ነበር፡፡ ቃል አክባሪ ሆነን የዛሬውን ዋና ርዕሰጉዳይ ከመጀመራችን በፊት ግን ሳንጠቅስ ያስተረፍናቸውን እና በሰኔው እትም ያዛነፍናቸውን እውነታዎች እናክም፡፡ በዚያውም ሐምሌ ጠብቁን ብለን ነሐሴ ላይ ስላመጣነው ክፍል2 ጽሁፍ እና ስለተፈጠረው ስህተት እኔ እና የመጽሔቱ አዘጋጆች የየድርሻችንን አንባቢዎቻችንን ይቅርታ እንለምናለን፡፡

Friday, June 23, 2017

ተወራራሽ የኪ-ነጥበብ ሥራዎች



ዘመናችንን በጥበብ ለመቃኘት የጀመርነውን ጉዞ ስንቀጥል የዛሬ ማረፊያችንን ተወራራሽ ጥበባት ላይ አድርገናል፡፡ በኪነ-ጥበቡ ዓለም አንድን ጥበባዊ ሥራ መነሻ በማድረግ፤ ወይም ሃሳቡን በሌላ ያልታየበት አቅጣጫ በማየት፤ ወይም ሙሉ ስራውን ወስዶ በሌላ የጥበብ ዘውግ መግለጽ እንግዳ ተግባር አይደለም፡፡

‹‹የማዕበል ዋናተኞች›› የተሰኘው የራዲዮ ድራማ ተዘፍኖለታል፡፡ ድርሰቱ የሐይሉ ጸጋዬ ነው፡፡ በወቅቱ ከፍተኛ ተደማጭነት የነበረው ሲሆን በበርካታ ታዳሚያን ልብ ውስጥ ለመግባት የቻለ ነበር፡፡ ድራማው ሲጠናቀቅ የዋናዋን ገጸባህሪ ስም ‹‹ዕፁብ ድንቅ›› ስያሜው በማድረግ ግሩም ዘፈን ተሰርቷል፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ያቀነቀነው ጎሳዬ ተስፋዬ ነው፡፡ ቆይቶ በላፎንቴኖችም ተዘፍኗል፡፡ በአሁኑ ሰዓት ደግሞ በቴሌቪዥን ተከታታይ ድራማነት መጥቷል፡፡ ተቀባይነቱ በራዲዮ የነበረውን ያህል መሆኑን ግን እጠራጠራለሁ፡፡

Monday, May 15, 2017

ቴዲ አፍሮ - ከ’አቡጊዳ’ እስከ ‘ኢትዮጵያ’


1993 . ለህዝብ በቀረበው ‹‹አቡጊዳ›› በተሰኘ አልበሙ የሙዚቃ አድማጭን ቀልብ ለመግዛት በቅቷል፡፡ ‹‹ያስተሰርያል›› ‹‹ጥቁር ሰው›› ‹‹ኢትዮጵያ››  የተሰኙ ወጥ የአልበም ስራዎችን እስካሁን አበርክቷል፡፡ ስለ ስራዎቹ ሲጠየቅ በዝርዝሩ ውስጥ የማያካትተው ስራም አለው፡፡ ‹‹ቴዲ›› ይሰኛል የአልበሙ መጠሪያ - አቦጊዳ ከተሰኘው አልበሙ በፊት ከኤክስፕረስ ባንድ ጋር የተሠራ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ሚሊንየም አካባቢ የወጣው አልበሙ 2 አዳዲስ ሥራዎችን እና ከመድረክ የተቀዱ ነባር ስራዎችን አካቶ ለገበያ የቀረበ ሥራው ነው፡፡ ተሰብስበው ቢጠረዙ ከአንድ አልበም የሚተርፉ ነጠላ ዜማዎችንም በተለያየ ጊዜ አበርክቷል፡፡