ለሰሩ ሰዎች፤ ልከኛ በሆነ መንገድ ተጉዘው የራሳቸውን
በጎ አሻራ ላኖሩ ጥበበኞች፤ ምስጋናን መቸር ተገቢ ነው፡፡ ለላቀው ጥበባቸው አድናቆት እና ሽልማት ማበርከት እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡
የዚህ ክዋኔ ግብረመልስ ከዋነኞቹ የአሁን ጥበበኞች በላይ ለከርሞ ተተኪዎች የጎላ ጠቀሜታ አለው፡፡ በጠንካራ ሥራዎቹ ሰበብ እውቅና
የተሰጠው፤ በላቀ አበርክቶው ምክንያትነት ምስጉን ለመባል የበቃ፤ . . . የጥበብ ዋርካ ሲበረክት አርዓያ የሚያደርጉት የነገ ፍሬዎች
ቁጥር እንዲያሻቅብ ያግዛል፡፡ ሁኔታው ለጠጥ ተደርጎ ሲታሰብ እንደ ሐገር እየተተካካን ሩቅ እንድንጓዝ የሚያስችለንን ነዳጅ የሚሞላልን
ግብአት ነው፡፡
Monday, December 11, 2017
Saturday, November 4, 2017
ኢትዮጵያዊነትን የምታስተጋባ አርቲስት - እጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ)
ሙዚቃ የዘመን ሥራ ነው፡፡ ዘመኑን ይመስላል፡፡ በድምፆቹ ዘመን
ን ያሳያል፡፡ በግጥም ሐሳቦቹ ጊዜ የወለደውን እሳቦት ይናገራል፡፡ የ1960ዎቹን የኢትዮጵያን ሙዚቃዎች የምንለየው በቅንብር መንገዳቸው (Orchestration) ነው፡፡ የ1970ዎቹንም እንዲሁ ከ60ዎቹ ከወሰዷቸው በጎ እሴቶች ጋር የራሳቸውን ደምረው (የተዉአቸው/ያልወሰዷቸው ታሳቢ ተደርገው) የበርካታ መሳሪያዎችን ድምፅ ማስደመጥ የሚያስችል የሙሉ ባንድ(Natural) የቅንብር ዘዬን በመከተላቸው ነው፡፡ እነ ሮሐ እነ ዋልያስ ባንዶችን መጥቀስ ይቻላል፡፡
ን ያሳያል፡፡ በግጥም ሐሳቦቹ ጊዜ የወለደውን እሳቦት ይናገራል፡፡ የ1960ዎቹን የኢትዮጵያን ሙዚቃዎች የምንለየው በቅንብር መንገዳቸው (Orchestration) ነው፡፡ የ1970ዎቹንም እንዲሁ ከ60ዎቹ ከወሰዷቸው በጎ እሴቶች ጋር የራሳቸውን ደምረው (የተዉአቸው/ያልወሰዷቸው ታሳቢ ተደርገው) የበርካታ መሳሪያዎችን ድምፅ ማስደመጥ የሚያስችል የሙሉ ባንድ(Natural) የቅንብር ዘዬን በመከተላቸው ነው፡፡ እነ ሮሐ እነ ዋልያስ ባንዶችን መጥቀስ ይቻላል፡፡
Wednesday, October 11, 2017
ከሳሽ የለም እንጂ፤ ተከሳሽስ ሞልቶ ነበር
ቀደም ባለው ጊዜ በሐገራችን የሚሰራጩ የሬዲዮ እና የቴሌቪዥን ጣቢያዎቻችን ቁጥር አነስተኛ ነበር፡፡ ከ 16ዓመት በፊት FM 97.1 ሳይጀመር፤ ጣቢያዎቹ የሚያስተላልፏቸው ፕሮግራሞች በህብረተሰቡ ዘንድ ያላቸው ተቀባይነት ደግሞ ከፍተኛ ነበር፡፡ የዕጅ ሰዓትን ለመሙላት ሳይቀር ማንጸሪያ እና መከራከሪያ ነጥቡ ከራዲዩ እኩል መሆኑ ነበር፡፡ አሁን በርከት ያሉ የራዲዮ ጣቢያዎች ባለቤት ነን፡፡ /የግልም የመንግስትም/ ለኢትዩጵያዊ ታዳሚ እንዲደርሱ ታልመው የሚሰናዱ የሳተላይትና የሀገር ውስጥ ቴሌቪዥን ጣቢያዎች ቁጥርም በማሻቀብ ላይ ነው፡፡ የተአማኒነቱ ጉዳይ ግን ቀስ በቀስ እየተሸረሸረ መጥቷል፡፡ ዛሬ ዛሬ በራዲዮ ድምጽን ማሰማት የጥቂት ደቂቃዎች ሙከራ ውጤት ነው፡፡ እንደቀደመው ዘመን ከፍ ያለ ትጋት አይጠይቅም፡፡
Wednesday, September 6, 2017
ከ ‹ፍቅር እስከመቃብር› የተነሱ ሌሎች ኪነ-ጥበባዊ ሥራዎች
በዘመን
እና ጥበብ መጽሔታችን የሰኔ ወር እትም ‹ተወራራሽ የኪነ-ጥበብ ሥራዎች› በሚል
ርዕስ ሥር መጨዋወታችን ይታወሳል፡፡
መነሻቸውን አስቀድሞ ለታዳሚ በደረሰ የኪነ- ጥበብ ውጤት ላይ ያደረጉ ሥራዎችን በወፍ በረር ቃኝተናል፡፡ ያነሱትን የጥበብ ውጤት፤
ቀድሞ የነበረውን እንደነበረ በሌላ የጥበብ ዘውግ፤ ወይም ነባሩን ይዘው በሌላ ዓዲስ የሀሳብ መንገድ የተገለፁትን ዘርዝረናል፡፡
በእግረመንገድ ያስተዋልነውን፣ በትውስታ ማህደራችን ቀድመው የተከሰቱልንን ብቻ አነሳስተናል፡፡
ወጋችንን ስናሳርግ ‹ፍቅር እስከ
መቃብር› የተሰኘው ረዥም ልብወለድ ላይ ተመስርተው የተሠሩትን ለማነሳሳት ቃል ገብተን ነበር፡፡ ቃል አክባሪ ሆነን የዛሬውን ዋና
ርዕሰጉዳይ ከመጀመራችን በፊት ግን ሳንጠቅስ ያስተረፍናቸውን እና በሰኔው እትም ያዛነፍናቸውን እውነታዎች እናክም፡፡ በዚያውም ሐምሌ
ጠብቁን ብለን ነሐሴ ላይ ስላመጣነው ክፍል2 ጽሁፍ እና ስለተፈጠረው ስህተት እኔ እና የመጽሔቱ አዘጋጆች የየድርሻችንን አንባቢዎቻችንን
ይቅርታ እንለምናለን፡፡
Friday, June 23, 2017
ተወራራሽ የኪ-ነጥበብ ሥራዎች
ዘመናችንን በጥበብ ለመቃኘት የጀመርነውን ጉዞ ስንቀጥል የዛሬ ማረፊያችንን ተወራራሽ ጥበባት ላይ አድርገናል፡፡ በኪነ-ጥበቡ ዓለም አንድን ጥበባዊ ሥራ መነሻ በማድረግ፤ ወይም ሃሳቡን በሌላ ያልታየበት አቅጣጫ በማየት፤ ወይም ሙሉ ስራውን ወስዶ በሌላ የጥበብ ዘውግ መግለጽ እንግዳ ተግባር አይደለም፡፡
‹‹የማዕበል ዋናተኞች›› የተሰኘው የራዲዮ ድራማ ተዘፍኖለታል፡፡ ድርሰቱ የሐይሉ ጸጋዬ ነው፡፡ በወቅቱ ከፍተኛ ተደማጭነት የነበረው ሲሆን በበርካታ ታዳሚያን ልብ ውስጥ ለመግባት የቻለ ነበር፡፡ ድራማው ሲጠናቀቅ የዋናዋን ገጸባህሪ ስም ‹‹ዕፁብ ድንቅ›› ስያሜው በማድረግ ግሩም ዘፈን ተሰርቷል፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ያቀነቀነው ጎሳዬ ተስፋዬ ነው፡፡ ቆይቶ በላፎንቴኖችም ተዘፍኗል፡፡ በአሁኑ ሰዓት ደግሞ በቴሌቪዥን ተከታታይ ድራማነት መጥቷል፡፡ ተቀባይነቱ በራዲዮ የነበረውን ያህል መሆኑን ግን እጠራጠራለሁ፡፡
Monday, May 15, 2017
ቴዲ አፍሮ - ከ’አቡጊዳ’ እስከ ‘ኢትዮጵያ’
በ1993 ዓ.ም ለህዝብ በቀረበው ‹‹አቡጊዳ››
በተሰኘ አልበሙ የሙዚቃ አድማጭን ቀልብ ለመግዛት በቅቷል፡፡ ‹‹ያስተሰርያል›› ፣ ‹‹ጥቁር
ሰው›› ፣ ‹‹ኢትዮጵያ›› የተሰኙ
ወጥ
የአልበም ስራዎችን እስካሁን አበርክቷል፡፡ ስለ ስራዎቹ ሲጠየቅ በዝርዝሩ ውስጥ የማያካትተው ስራም አለው፡፡ ‹‹ቴዲ›› ይሰኛል
የአልበሙ መጠሪያ - አቦጊዳ ከተሰኘው አልበሙ በፊት ከኤክስፕረስ ባንድ ጋር የተሠራ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ሚሊንየም አካባቢ የወጣው አልበሙ 2 አዳዲስ ሥራዎችን እና ከመድረክ የተቀዱ ነባር ስራዎችን አካቶ ለገበያ የቀረበ ሥራው ነው፡፡ ተሰብስበው ቢጠረዙ ከአንድ አልበም የሚተርፉ ነጠላ ዜማዎችንም በተለያየ ጊዜ አበርክቷል፡፡
Saturday, April 22, 2017
ተናጋሪ ፖስተሮች
ማስታወቂያ
ሰፊ ጽንሰ ሐሳብ ነው፡፡ በርካታ ዘርፎችም አሉት፡፡ የራሱ የክዋኔ ስርዓት እና ብልሃትም እንዲሁ…ከዚህ ሰፊ ባህር አንዲት ቀጭን
ሰበዝ መዘን ለዛሬ ጨዋታችን የሃሳብ ምህዋር መሽከርከሪያነት ልንፈቅድ ነው፡፡
በአንድ ወገን አድጓል በሌላው
አላደገም፤ በአንዱ ጎጥ ኢንዱስትሪ ነው በሌላው አይደለም፤ በአንዱ ጎራ ባህል አጥፍቷል በሌላው ይገነባል . . . እያስባለ በማከራከር ላይ ስላለው የኢትዮጵያ ፊልም ከፊልምም ስለ ፖስተሮች
/የስዕል ማስታወቂያዎች/ እናውጋ
ማሳወቅ፣ ለተጠቃሚነት መገፋፋት (ማጓጓት)፣ ዘላቂ ደንበኛ ማድረግ -ዋና ዋናዎቹ
የማስታወቂያ ዓላማዎች ናቸው፡፡ በርግጥ በማስታወቂያ ዙሪያ ስምምነት ላይ ያልተደረሰባቸው ጉዳዮች አሁንም አሉ፡፡ ማስታወቂያ ሳይንስ
ነው ወይስ ጥበብ፤ ዓላማው ማታለል፣ ማሳመን፣ ወይስ ማስገደድ . . .ሌሎችም ቁርጥ ያለ ምላሽ ያልተሰጣቸው ሃሳቦችን ከነክርክራቸው
አሁንም እንደተሸከመ ነው፡፡
Friday, January 13, 2017
መልክን የሻሩ ዘፈኖች
እያንዳንዳቸው የጥበብ ስራዎች የተሰሩበትን ዘመን አስተሳሰብ፣ ምኞት እና አኗኗር የሚያሳዩ መስታወቶች ናቸው፡፡
‹‹ፈረንጅ ሃገር ሳትሄድ ገና እዚሁ ሳለህ
የገባኸውን ቃል እንዴት ታፈርሳለህ?
የእውነት ሰው መስለኸኝ ክቡር የከበረ
ቃልኪዳኔን ይዤ ጠብቄህ ነበረ ››
የሚለው በብዙነሽ በቀለ የተዜመ ግሩም ዘፈን ብዙ ወጣቶች ለትምህርት ወደ ውጪ ሃገራት የሚሄዱበት፤ ትምህርታቸውን አጠናቀው በሚመለሱበት ጊዜ ደግሞ በአስተሳሰብ ልዩነት ወይም በሌላ የራሳቸው ምክንያት ከቀድሞ ወዳጆቻቸው የሚለያዩበት እንደነበረ መገመት ይቻላል፡፡
Subscribe to:
Posts (Atom)