እያንዳንዳቸው የጥበብ ስራዎች የተሰሩበትን ዘመን አስተሳሰብ፣ ምኞት እና አኗኗር የሚያሳዩ መስታወቶች ናቸው፡፡
የሚሉት ዘፈኖች ሌላ የዘመን መስታወቶች ናቸው፡፡ የወቅቱን ስእል ቁልጭ አድርገው የሚያሳዩ…
አንዱ ማሬ ማሬ ብሎ ከተጨበጨበለት የሁሉም ዘፋኝ የውበት መግለጫ ማር ይሆናል፡፡አንዷ የደቡብ ምት ያለውን ዜማ ሰርታ ጆሮ ካገኘች የደቡብ ምት ጎርፍ የዘፈን ሜዳውን ይሞላዋል፡፡ ሌላው ማታ ማታ ብሎ ዘፍኖ በተደጋጋሚ ከተሰማ የማታ ማታ ባዮች ቁጥር ያሻቅባል፡፡ አንዱ ‹ት-ሬጌ› /ትግርኛ እና ሬጌ/ ሲል ‹ባቲ እና ብሉዝ›፣ ‹ሬጌ-ከሚሴ›፣ ‹አገውኛ ወላይቲኛ›፣ ‹ቺ-ጌ› /ችክችካ እና ሬጌ/ እያለ የመናጆ ሰልፉ ይቀጥላል፡፡ አንዱ 70 ደረጃ ብሎ ዘፍኖ አድናቆት ሲጎርፍለት ሌላው ቀበና፣ ሺ ሸማኒያ እያለ ይቀጥላል… መለኪያው ጭብጨባ እና ጭብጨባ ብቻ ነው፡፡ ምነው ሳይነካኩ በተውት አስብለው የሚያስቆጩ በርካታ የዘፈን ግጥም ሀሳቦች ይገጥማሉ፡፡
ዘሪቱ ከበደ ከውብ ድምፅ እና የአዜያዚያም ዘይቤ በተጨማሪ የተባ ብእር የታደለች አርቲስት ነች፡፡ የዘፈኖቿን ግጥምና ዜማ ራስዋ ታሰናዳቸዋለች፡፡ በግሌ የአቅሟን ያህል እየሰራች ነው ብዬ ባላምንም በሰጠችን አንድ አልበም እና በጥቂት ነጠላ ዜማዎቿ ላይ የተካተቱት የግጥም ሀሳቦች ከፊሎቹ ከዚህ ቀደም በዘፈን ያልተነሱ፤ ገሚሶቹ ከጥንካሬያቸው የተነሳ እንደምን ስትል ይህን ሀሳብ ለዘፈን መዘዘች የሚያስብሉ፤ የተቀሩት ደግሞ ከዚህ በፊት ብዙ የተባለባቸውን ከማለት በላይ በሆነ ገለፃ የተራቀቀችባቸው ናቸው፡፡
መባልን ሲሰማ ላደገ የሚጎረብጥ ሀሳብ ቢመስልም ከእውነታው ሲናጸር ግን ሁልጊዜ አይሰምርም፡፡
ይባልላታል፡፡ ቦታ ሲለዋወጡ ታዘባችሁልኝ? በአእላፍ ዘፈኖቻችን እንዳደመጥነው ፍቅርን መልክ አልወለደውም፡፡ አፍዞ የሚያስቀር ቁንጅና አይደለም ገጣሚን ነሽጦ ብእር ያስጨበጠው፡፡ ደብዛዛ ውበት ነው አንጂ፤
የሚለው የጌቴ አንለይ ዘፈን በመድሀኒትነት የሚከሰተው ይህን ጊዜ ነው፡፡ ‹‹መልክሽ አይበልጥሽም›› ከሚል ዘፈኑ ላይ፡፡ ይህ የመጨረሻ አልበሙ /ለጊዜው ለማለት እንጂ ከንግዲህ አይዘፍንም ለማለት አይደለም፡፡/ በግጥም ረገድ ጥሩ ጥሩ ሀሳቦችን ያነሳበት ስራው ቢሆንም አድማጭ ዘንድ የነበረውን ተደማጭነት ግን እጠራጠራለሁ፡፡
© ዘመን እና ጥበብ መፅሔት መጋቢት 2009 ዓ.ም ላይ የወጣ
‹‹ፈረንጅ ሃገር ሳትሄድ ገና እዚሁ ሳለህ
የገባኸውን ቃል እንዴት ታፈርሳለህ?
የእውነት ሰው መስለኸኝ ክቡር የከበረ
ቃልኪዳኔን ይዤ ጠብቄህ ነበረ ››
የሚለው በብዙነሽ በቀለ የተዜመ ግሩም ዘፈን ብዙ ወጣቶች ለትምህርት ወደ ውጪ ሃገራት የሚሄዱበት፤ ትምህርታቸውን አጠናቀው በሚመለሱበት ጊዜ ደግሞ በአስተሳሰብ ልዩነት ወይም በሌላ የራሳቸው ምክንያት ከቀድሞ ወዳጆቻቸው የሚለያዩበት እንደነበረ መገመት ይቻላል፡፡
‹‹ ወልደሽ ያሳደግሺኝ
እናቴ ናፈቅሺኝ ››
በሚሉት ስንኞች የተገነባው የድምፃዊ አያሌው መስፍን ዘፈን ደግሞ ቤተሰቤን ልርዳ ብለው ከገጠር ወደ ከተማ የፈለሱ የወቅቱን ዘመነኞች በእንባ ያራጨ ዘመንን ተራኪ ዘፈን ነው፡፡
‹‹ፓሪ ሞድ ለብሳለች
ሹራብ ደርባለች
ጸጉሯን ተተኩሳ ለፎርም ሰዓት አድርጋለች›› ….
የሚለው ዘፈንና
‹‹እራስዋን ሹሩባ ተሰርታው ብትመጣ
ዐይኗን በቀጭኑ ተኩላው ብትመጣ
ጥርሷን ጉራማይሌ- ተነቅሳው ብትመጣ
ሳልታመም ሞትኩኝ ሳልሞት ነፍሴ ወጣ››
የሚሉት ዘፈኖች ሌላ የዘመን መስታወቶች ናቸው፡፡ የወቅቱን ስእል ቁልጭ አድርገው የሚያሳዩ…
እያነቡ እስክስታ፣ በወረቀት የሰው በደም ያንቺ ናቸው፣ አንቺ የሌለሽ ጊዜ ዓይነቶቹ ደግሞ በርካቶች ራስን ለመለወጥ ከሀገር የሚወጡበት ዘመን የማህበረሰብ እንጉርጉሮዎች ናቸው፡፡
ፊቸሪንግ በዘፈኖቻችን ላይ የበረከተበት እና እያንዳንዱ የዘፈን አልበም ላይ ቢያንስ አንድ ፊቸሪንግ ይካተት የነበረበት የዘጠናዎቹ መጀመሪያ ዘመን ከ FM ጣቢያዎች መስፋፋት እና በዚያም በርካታ ዲጄዎች የውጪ ዜማዎችን ለህዝብ ማሰማታቸው፤ ኢንተርኔት በቀላሉ መገኘት ከመቻሉ . . . ጋር ተያይዞ ለውጪ ሙዚቃዎች የነበረንን ተጋላጭነት እና የመሳብ ሁኔታን ያሳያል፡፡
ነገሩ ጠለቅ ያለ ጥናት እና በርከት ያሉ ማስረጃዎችን እንደሚፈልግ እንደተጠበቀ ሆኖ ማለት ነው፤
በኔ የወፍበረር ግምገማ አሁን ያለነው የመናጆ ዘመን ላይ ይመስለኛል፡፡ በተቀደደ ቦይ የመፍሰስ፤ የራስን መንገድ ያለመፈለግ ዘመን፡፡
አንዱ ማሬ ማሬ ብሎ ከተጨበጨበለት የሁሉም ዘፋኝ የውበት መግለጫ ማር ይሆናል፡፡አንዷ የደቡብ ምት ያለውን ዜማ ሰርታ ጆሮ ካገኘች የደቡብ ምት ጎርፍ የዘፈን ሜዳውን ይሞላዋል፡፡ ሌላው ማታ ማታ ብሎ ዘፍኖ በተደጋጋሚ ከተሰማ የማታ ማታ ባዮች ቁጥር ያሻቅባል፡፡ አንዱ ‹ት-ሬጌ› /ትግርኛ እና ሬጌ/ ሲል ‹ባቲ እና ብሉዝ›፣ ‹ሬጌ-ከሚሴ›፣ ‹አገውኛ ወላይቲኛ›፣ ‹ቺ-ጌ› /ችክችካ እና ሬጌ/ እያለ የመናጆ ሰልፉ ይቀጥላል፡፡ አንዱ 70 ደረጃ ብሎ ዘፍኖ አድናቆት ሲጎርፍለት ሌላው ቀበና፣ ሺ ሸማኒያ እያለ ይቀጥላል… መለኪያው ጭብጨባ እና ጭብጨባ ብቻ ነው፡፡ ምነው ሳይነካኩ በተውት አስብለው የሚያስቆጩ በርካታ የዘፈን ግጥም ሀሳቦች ይገጥማሉ፡፡
ከዚህ የመናጆ ሰልፍ ያፈነገጡትን፣በአንድ ዓይነት ምህዋር ላይ ላለመሽከርከር የቆረጡትን፣ባልተሄደበት መንገድ የተራመዱትን፣ ለመመልከት በቁፈራ ላይ ነን ተከተሉኝ፡፡
በዘፋኞቻችን ጉሮሮ ተደጋግሞ የሚቀነቀነው ‹ፍቅር› ከደምግባት ጋር ብቻ ተሳስሮ ሲኖር ታዝበው - ‹ሌላም መንገድ አለ!› ብለው የታደጉትን አበጃችሁ ልንል ነው፡፡ በአያሌ ዘፈኖቻችን ውስጥ ለዘመናት የተጓዘበትን መንገድ ጥለው ውበትን ከፍቅር ነጥለው ያሳዩንን ዘፈኖች ልንመለከት ነው፡፡ ፍቅር ያስውባል፣ ፍቅር ከአካላዊ ውበት በላይ ነው፡፡ ያሉንን የዘፈን ስንኞች ልንዘርዝር
‹‹ሚስትህ በጣም ፉናጋ ናት - ፉንጋ ከኔ የባሰች
አንተን መሳይ አደላት - ቀድማ ስላልፈረደች
አንተ በጣም ቆንጆነህ - በሚያነጋግር ዓይነት
በውነት ግራ ይገባል - አንተን ከሷጋር ማየት››
/ዘሪቱ ከበደ/
ዘሪቱ ከበደ ከውብ ድምፅ እና የአዜያዚያም ዘይቤ በተጨማሪ የተባ ብእር የታደለች አርቲስት ነች፡፡ የዘፈኖቿን ግጥምና ዜማ ራስዋ ታሰናዳቸዋለች፡፡ በግሌ የአቅሟን ያህል እየሰራች ነው ብዬ ባላምንም በሰጠችን አንድ አልበም እና በጥቂት ነጠላ ዜማዎቿ ላይ የተካተቱት የግጥም ሀሳቦች ከፊሎቹ ከዚህ ቀደም በዘፈን ያልተነሱ፤ ገሚሶቹ ከጥንካሬያቸው የተነሳ እንደምን ስትል ይህን ሀሳብ ለዘፈን መዘዘች የሚያስብሉ፤ የተቀሩት ደግሞ ከዚህ በፊት ብዙ የተባለባቸውን ከማለት በላይ በሆነ ገለፃ የተራቀቀችባቸው ናቸው፡፡
በነጠላ ዜማነት የሰማነው ‹‹የወንድ ቆንጆ›› የተባለው የግጥም ሀሳብ ከላይ ከዘረዘርነው ‹በዘፈን ያልተነሱ› ሀሳቦች መሀከል ልንመድበው የምንችል አስገራሚ ሀሳብ ያዘለ ዘፈን ነው፡፡
በግጥሙ ውስጥ 3 ባለታሪኮች ተስለዋል፡፡ 2 ሴት እና 1 ወንድ፡፡ ሁለት ፉንጋ ሴቶች እና አንድ ቆንጆ ወንድ፡፡ ተራኪዋ ሴት ናት፡፡ ፉንጋ መሆንዋን እምታውቅ፤ የመልኳን ደረጃ ተረድታ ሰውን በመልኩ የምትሰፍር፤ መጽሀፍን በሽፋኑ የምትመዝን አላዋቂ … ፍቅርን ብሎ ፍቅርን ሽቶ ‹‹ይህ አለኝ! ይህ የላትም›› ሳይል የቀረባትን ወንድ ማህበረሰቡ ባሳደረባት የአስተሳሰብ ተጽእኖ ምክንያት ‹‹ወግድልኝ!›› ለማለት የምትደፍር የዋህ
‹‹ወደኋላ መለሰኝ - አሳሰበኝ ስለኛ
የጀማመርከኝ - ሰሞን እንድሆንህ ፍቅረኛ
ቆንጆ ወንድ ማፍቀር ትርፉ - እርም ብዬ መከራ
ግዴን ተከላክዬህ - ኮራሁብህ ሳትኮራ
ልቤ ፈራ ፈራ
ደሞ የወንድ ቆንጆ››
እያለች የምታንጎራጉር . . . ተወኝ ስትለው ትቷት፣ ሂድልኝ ስትለው ሰምቶ ካጠገቧ ርቆ ሄዋኑን ያገኘ:: የቀድሞ አፍቃሪዋ የሆነ ባለትዳር ወንድ ላይ ከዳር ቆማ እንድትቀና፣ ትላንቷን እንድትመለከት ያደረጋት የሚስቱ ፉንጋነት ነው፡፡ ከሷ የባሰች ፉንጋ መሆኗ
‹‹እሷግን አመነችህ - ትንሽነት ሳይሰማት
ፉንጋ ሳለች ስታምርህ - ተማምና እንደምትገባት››
ትለዋለች፡፡ እኔ መልክ አይቼ ስመለስ፣ ውስጥህን ሳላይ ስሳሳት፣ በኖረ ልማድ ስወሰድ፣ ደሞ የወንድ ቆንጆ በሚሉት ብሂል ስታለል እሷ ግን…. ትልላታለች፡፡
‹‹ቆንጆ ወንድ ማፍቀር ትርፉ - እርም ብዬ መከራ
ግዴን ተከላክዬህ - ኮራሁብህ ሳትኮራ
ሲባል እማውቀው - ልቤም ሲፈራ
እንዳልጎዳ ብዬ - አንተም እንዳትኮራ
ልቤ ፈራ ፈራ››
በውብ ስንኞች የተገነባው የዘፈን ግጥም የሚጠናቀቀው ፉንጋ ተብላ ስትገለጽ የነረችውን እንስት ቆንጆ በማለት ነው፡፡ዘሪቱ በግጥሟ ይህንን ያደረገችው በስህተት አይደለም፡፡ ሆን ብላ ነው፡፡ ተራኪዋ ገጸባህሪ እኔ ባይ ተራኪ- ስህተቷን ስትረዳ፣ ፍቅርን በመልክ ሚዛን መስፈሯን ስትተው ሸውራራ እይታዋ ይታረቃል፡፡ ያኔ ከደምግባት በላይ ማሰብ ትጀምራለች፡፡ ፉንጋነት ይምታታባታል፡፡ ‹ኧረ እስዋም ቆንጆ ናት› ትላታለች፡፡
‹‹ሎጋ ለሎጋ
ሲያወጋ ነጋ
ቆንጆ ለቆንጆ
ይሰራል ጎጆ›› …
መባልን ሲሰማ ላደገ የሚጎረብጥ ሀሳብ ቢመስልም ከእውነታው ሲናጸር ግን ሁልጊዜ አይሰምርም፡፡
ቀጣይ ማረፊያችን ኢዮብ መኮንን ነው፡፡ /ነፍስ ይማር/ መጀመሪያ አልበሙ ውስጥ የተካተተው እና ኤሊያስ መልካ ፅፎ ያቀናበረው ‹‹ደብዝዘሽ››
ኤልያስ መልካ የሚለው ስም ከ10 ለሚበልጡ ዓመታት በኢትዮጵያ ሙዚቃ ላይ ነግሶ ቆይቷል፡፡ ጀማሪ ሙዚቀኞች በርሱ በኩል ካለፉ የህዝብን ልቡና መቆጣጠር አይሳናቸውም፡፡ ቴዲ አፍሮ፣ ሚካያ በሀይሉ፣ ዘሪቱ ከበደ፣ ኢዮብ መኮንን ለዚህ ተጠቃሾች ናቸው፡፡ ለአንጋፋዎቹም ከመሀሙድ፣ ኩኩ፣ አስቴር እና ሌሎችም ጋር ሰርቷል፡፡
በቅንብር ከሰራቸው አንጻር በቁጥር ያልበዙ ይሁኑ እንጂ የግጥም ስራዎችም አሉት፡፡ ድንቅ ሀሳቦችን ያዘሉ ምርጥ ስንኞችን ለዘፈኖቻችን አቀብሏል፡፡ በ ኢዮብ፣ በ ቤሪ፣ በ ጌቴ አንለይ በኩል፡፡
ድምፅ ጩኸት ብቻ ነው፡፡ ድምቀት መብለጭለጭ ብቻ ነው፡፡ ደስታ ሳቅ ብቻ ነው፡፡ ባዮችን የመከተበት ሌላም መንገድ አለ ያለበት ዘፈን ነው ደብዝዘሽ፡፡ ልብ ባንልም - የምንኖረውን እውነታ የገለጠ
‹‹መልክን የሻረ
አንቺጋ ምን ተሻለ
ከሩቅ ሳትስቢ
አየሁ ልቤ ስትገቢ . . .››
ብሎ ይጀምራል፡፡
‹‹ካንቺ በላይ ቆንጆ ሞልቶ
ያውቃል ልቤ ቀርቦም አይቶ
ግን በምን በለጥሻቸው?
ቆንጆዎቹን አስናቅሻቸው?
ደብዝዘሽ አጋለጥሻቸው? . . .››
ብሎም ይጠይቃል፡፡ይህች የሚዜምላት ሴት ማህበረሰቡ ባስቀመጠው የቁንጅና ደረጃ ላይ ከፊት የለችም፡፡ ከሩቅ አትስብም፡፡
‹‹አይነ ኮሎ - ሽንጠ ሎጋ የወለዱ እንደሆን
ታመጣለች አማች ብረት መዝጊያ እሚሆን … ››
የሚባልላት አይደለችም፡፡ ወንዱን ሁሉ በውበቷ አንበርክካ የኔነች የኔነች ዱላ ያማዘዘች አይደለችም፡፡
‹‹ካንቺ በላይ ውበታቸው
ካንቺ በላይ እውቀታቸው
ስቄም ነበር በቀልዳቸው
ግን በምን በለጥሻቸው ? …››
ይህ ሁሉ ቢሆንም ከልብ ትገባለች፡፡ ይባስ ብላ ልኬት ማበጃ ትሆናለች፡፡ አንቺን ካልተስተካከለች የታል ቁንጅናዋ ታስብላለች፡፡ መልከ መልካምነትን ታስረሳለች
‹‹ምንድነው ብርቅ ሆኖ የሚያስወድደኝ
ሁሉሽን እንዳደንቅ የሚያስገድደኝ
ቆንጆም ውብም ለኔ ያንቺ አይነት ብቻ
ባይም ልቤ አያምንም እንዳለሽ አቻ …››
ይባልላታል፡፡ ቦታ ሲለዋወጡ ታዘባችሁልኝ? በአእላፍ ዘፈኖቻችን እንዳደመጥነው ፍቅርን መልክ አልወለደውም፡፡ አፍዞ የሚያስቀር ቁንጅና አይደለም ገጣሚን ነሽጦ ብእር ያስጨበጠው፡፡ ደብዛዛ ውበት ነው አንጂ፤
አንዲት ስሟ የተዘነጋኝ የሜዳ ቴኒስ ተጫዋች በአንድ ቃለመጠይቋ እንዲህ ብላ እንደነበር መስማቴን አልዘነጋሁም
‹‹ በርካታ ሰዎች ከሜዳ ውጪ ሲያገኙኝ ስለችሎታዬ ሳይሆን ስለ ቁንጅናዬ ይነግሩኛል፡፡ እኔ እምፈለወገው ግን ስራዬን እንዲያስበልጡልኝ ነው፡፡ ››
ነገሩ ቅብጠት ይመስል ይሆናል፡፡ በባለቤቱ ጫማ ላይ ሆኖ ሲታይ ግን ህመሙ ይታወቃል፡፡ ለፍተው ጥረው ካመጡት፣ መሆን እና ማድረግ ከሚፈልጉት ነገር በላይ - ለመኖሩ ምንም አስተዋጽኦ ባላደረጉበት ነገር መጠራት፣ ሙሉ ምስጋናውን ተፈጥሮ ብቻ በምትወስደው፣ ምንም ባልጣረችለት ስጦታ መመስገን፣ በታደሉት እንጂ ባልታገሉለት መሞገስ . . .
‹‹ቢደምቅም ባይደቅም - ቢበርደው ቢሞቀው
ላይሽ ብቻ አይደለም ልቤን የደነቀው
መች ዐይኔስ ሆነና ከላይ አይቶሽ ብቻ
መች ድሮስ ሆነና ካንገት በላይ ምርጫ
ልቤ አንቺን እንጂ መች መልክሽን ብቻ
መች አየ እሱን ብቻ››
የሚለው የጌቴ አንለይ ዘፈን በመድሀኒትነት የሚከሰተው ይህን ጊዜ ነው፡፡ ‹‹መልክሽ አይበልጥሽም›› ከሚል ዘፈኑ ላይ፡፡ ይህ የመጨረሻ አልበሙ /ለጊዜው ለማለት እንጂ ከንግዲህ አይዘፍንም ለማለት አይደለም፡፡/ በግጥም ረገድ ጥሩ ጥሩ ሀሳቦችን ያነሳበት ስራው ቢሆንም አድማጭ ዘንድ የነበረውን ተደማጭነት ግን እጠራጠራለሁ፡፡
ለመልኳ ምንም የማይወጣላት ገጸባህሪ እዚህ ዘፈን ውስጥ አለች፡፡ ልቅም ካለው መልኳ በላይ በእሷነቷ፤ መርጣ ባመጣችው ማንነቷ፤ ሊመዝናት የሚሻ አፍቃሪዋ እንዲህ ያንጎራጉርላታል፡፡
‹‹መች እተውሽ ነበር ዐይኔ እስኪያይሽ ድሮ
ባይኖር እንኳን መልክሽ ውብ ባትሆኚም ኖሮ
ከላይ እዩኝ ባለች ባደባባይቷ
አንቺ አትመዘኚም በብልጭልጪቷ
ውብ ቢሆን በርግጥም
መልክሽ ካንቺ አይበልጥም
ምን ቢሆን ከውጪ አንቺ አትለወጪም፡፡››
እያለ ከመልክ ውጪ ያለ ማንነት እንደሚያፈዝ፣ በውበት መዝገበ ቃላት ላይም እንዳለ እና እንደነበረ፣ ይነግረናል፡፡ በጌቴ አንለይ ስርቅርቅ ድምጽ እየተዋዛ አስተሳሰባችንን ይቃኛል፡፡
‹‹ለኔ አዲስ ነሽ ውዴ
በጄ እስክትገቢልኝ - እስከሚያቅፍሽ ክንዴ
አይደለም መውደዴ . . .››
እያለ ከጊዜያዊ ሙቀት በላይ ያደገውን የፍቅሩን መግለጫ ያቀርባል፡፡ ይህ ብቻ አይበቃውም ውስጣችን የኖረውን የውበትን ብያኔ ሊያፈራርሰው ይጥራል፡፡
‹‹ጊዜ ሲለዋወጥ ወራቱ ሲጨምር
ይነጥፍ የለም ወይ ውበት ቢሆን ጸጉር
እንኳን ሲበስልና የድሮ ቀን ሲከብደው
መልክማ ይቀየራል ላንዳፍታም ቢበርደው
ላዩማ ሀላፊ ነው መልና ደምግባት
ሁሌም ግን አያልፍም ብርቅ የልብሽ ውበት›
የጥላሁን ገሰሰ እና የብዙነሽ በቀለ ቆየት ያለ ‹‹እሺ በይ›› የተሰኘ የቅብብል ዜማ እዚህ ላይ ሳይጠቀስ መታለፍ የሌለት ነው፡
አቤት አይንሽ አቤት ጥርስሽ ውበቱ
ልብ ይሰውራል ልዩ ነው ፍጥረቱ
ልብሽ ጨካኝ ነው መቼም አይበገር
ኧረ አንቺ ልጅ ወይ ብትይኝ ምን ነበር ….
እያለ ለዛ ባለው ዜማ ሲያዋያት እንዲህ ስትል ትመልስለታለች፡፡
‹‹ስላይኖቼና ጥርሶቼ ቁንጅና
አትጨነቅ ያምላክ ስራ ነውና››
መለወጥ በምችለው፣ ፈልጌ ባለጣሁት ነገር ላይ እንነጋገር የሚል ዓይነት ስሜት አለው፡፡ ያምላክ ስራ ነው የኔ እጅ የለበትም፡፡
ሌላው ተጠቃሽ ሰይፉ ዮሐንስ ነው፡፡ የዘፈኑ ርእስ ‹‹እመቤትነትሽ›› ይሰኛል፡፡ የአክብሮቴ ሚዛን የሚለካው፣ የፍቅሬ ጥልቀት የሚመተረው፣ አድናቆቴ የሚመነጨው በመልክ መስፈሪያ አይደለም፡፡ በዝና ሜትር አይደለም፡፡ ይለናል በስንኞቹ - እነሆ የስንኙ ድርድር
‹‹በመልክሽ አይደለም ውበትሽን የማውቀው
በዝናሽ አይደለም ስምሽን የማደንቀው
በጨዋነትሽ ነው በውነተኛነትሽ
ያንቺ ትልቅነት እመቤትነትሽ›
አስቴር አወቀም ያነሳነውን ርዕሰ-ጉዳይ የተመለከተ ዘፈን በውብ ለስላሳ ድምጽዋ አቀንቅናለች፡፡ እንዲህ ስትል ...
‹‹ከሁሉም ከሁሉም ጎልቶ የሚታየኝ
ዘወትር እንድወድህ የሚያስገድደኝ
አይደለም ገንዘብህ ወይም ውበትህ
ግሩም ጸባይህ ነው የኔ ያረገህ››
ለመሰናበቻ የ ታምራት ሞላን እናንሳ
‹‹አፍንጫ ምን ቢቆም ቢገተር
በረዶ ጥርስ ቢደረደር
ተረከዝ ባትና ቁመና
መች አይቶ ልቤ ፈለገና
መልኳ መጠነኛ ቁመቷም አጭር ነው
የተዋደድንበት ነገሩ ሌላ ነው››
የዛሬውን ጨዋታ እዚህ ላይ ስናበቃ በሌላ ጥበባዊ ወግ እንደምንገናኝ ተስፋ እናድርግ፡፡ ቸርሁኑልኝ!
© ዘመን እና ጥበብ መፅሔት መጋቢት 2009 ዓ.ም ላይ የወጣ
No comments:
Post a Comment