Wednesday, August 28, 2013

በመካነ ፊት (facebook) መንደር በዓጭር ጊዜ ውስጥ ታዋቂ ጦማሪ ለመሆን የሚያስችሉ 5 ነጥቦች


ክቡር ጦማሪ ሆይ፡- መቼም በሆነ የታሪክ አጋጣሚ ዘመኑ በፈቀደልን ስሜትን የመግለጫ፣ ሀሳብን የማስተላለፊያ መንገዶች በመጠቀም የልባችንን መተንፈስ ከጀመርን ሰነባበተ እነሆ እኔም ሳይገባኝ ወደላይ ተንጠራርቼ ምክር ለመለገስ ዳዳኝ። አንተም እንደምታውቀው ባለፈው ጊዜም ፓስት አድርገህ እንዳየሁት <<ሰዎች ለሰዎች ያለስስት የሚለግሱት ነገር ምክር ነው!>> እናም ታናሽነቴን ሳታይ የምለውን እንደምትቀበለኝ ተስፋ አደርጋለሁ።

1ኛ- የህዝቡን የልብ ትርታ አዳምጥ፡-
 
ሰሞነኛ ትኩሳቶችን እየተከታተልክ የሚመስልህን ነገር በፍጥነት እና በተከታታይ በገፅህ ላይ ማስፈር ተገቢ ነው። ነገርየው የምታምንበት ባይሆንም እንኳን አጋጣሚው በርካታ 'ላይኮች'ን ሊያስገኝልህ ስለሚችል ተመሳሳይ ገጠመኞችን በቀላሉ ማለፍ አይገባም። የፖለቲካም ሆነ የሀይማኖት፤ የሀገር ውስጥም ሆነ የውጭ ፤የኪነጥበብም ሆነ የእስፖርት፤ የግለሰብም ሆነ የድርጅት፤ የቡድንም ይሁን የተቋም ሰሞነኛ ወሬዎችን አትለፍ። ፍላጎት የለኝም፣ ስለጉዳዩ የማውቀው ነገር የለም፣ በቂ መረጃ አልሰበሰብኩም ወዘተ … የሚሉ ተልካሻ ምክንያቶችን አስወግድ ብታውቅም ባታውቅም ቢጥምህም ባይጥምህም ብታምንበትም ባታምንበትም ፃፍ።

2ኛ ደፋር ሁን፡- 

Monday, August 26, 2013

አበል ለዘላለም ትኑር!


የሀይስኩል ተማሪ በነበርኩበት ጊዜ ነው። በእድሜ ገፋ ያሉት መምህር እጃቸው በቾክ ተጨማልቆ - ብላክቦርዱን መለየት በማይቻሉ እና በተዘበራረቁ መስመሮች፣ ቅርጾች፣ ቁጥሮች፣ ፊደላት አጨማልቀው እያስተማሩ ነው። እያስረዱ ነው። የተማሪው ፊት ላይ የተመከቱት ሁኔታ ግን እንዲቀጥሉ የሚገፋፋ አልነበረም። ተማሪው ፊት ላይ ድብርት ይነበባል። መምህሩ በድንገት ማስረዳታቸውን አቁመው ያልተለመደ ጥያቄ ጠየቁ

“ይህንን ትምህርት መማራችሁ ለምን ይጠቅማችኋል?” ጉዳዩ በክፍሉ መነቃቃትን ፈጠረ። “ግን ይሄ ሳብጀክት ለምን ይጠቅማል?”

መምህሩ እጅ ያወጣን ተማሪ ብቻ ሳይሆን አርፎ የተቀመጠንም ማፋጠጥ ይዘዋል።
“ይህንን ሳብጀክት ለምን ትወስዳላችሁ? ህይወታችሁ ላይ ምን ይጨምራል?”
ነገርየው አሳፋሪ ቢሆንም ከ50 የሚበልጠው እና ደብተሩ ላይ እየጻፈ፣ መፅሀፍ እያነበበ፣ ሰዓት ጠብቆ እየገባ፣ እያጠናና እየተፈተነ የሚወስደውን ኮርስ ምን እንደሚጠቅመው አያውቅም።
መምህሩ ንዴት፣ ብስጭት፣ መገረም እጠየተነበበባቸው ይዘውት የመጡትን ጓዝ ሸክፈው ወደመውጫው በር አመሩ። 

Thursday, July 18, 2013

ክር ባጭር

በድሮ ጊዜ ነው። በሀገር ወግ በህግና በስርዓትያሳደጓትን ልጃቸውን ላግባ ባይ ጠያቂ የበዛባቸው አባወራ ማንን ከማን ለይተው ለማን እነደሚድሯት ግራ ቢገባቸው ፈተና አዘጋጁ

ፈተናው ጋቢ መስፋት ነው። አስፈላጊው መሳሪያ ሁሉ ተሟልቷል። ጋቢ፣ ክር. መርፌ ሁሉም ቀርቧል።

ያፈቀራትን ሴት በእጁ ለማስገባት የጓጓው የአዳም ዘር ውድድሩን ጀመረ። ሁሉም ጥድፊያ ላይ ነው። ማንም ማንንም አያይም። አባት እና ልጅ ብቻ ሁኔታውን ያታዘባሉ።

Thursday, May 2, 2013

ምኞት



እንደ ጎጆዬ ድባብ
                 እንደከባቢው አንድምታ
እንረታሰረች ምላሴ
                  እንዳለሁበት ሁኔታ
ዙርያዬን አቅፎ እንደያዘኝ
                 እንደሚስተዋል እይታ
ቀን ይናፍቀኛል
ማየት ያሰኘኛል 
ውስጥ የማያጮህበት
                ዝም ያለ ዝምታ።

ለካ…



ከመነጨበት የጨው ባህር ይከተታል ተመልሶ
እንባም ለካስ ይዋጣል ያታመቃል ለካስ ለቅሶ

Monday, April 29, 2013

ሰስፔንድድ ኮፊ



"ሰስፔንድድ ኮፊ" ስለሚባል ነገር ሰምቼ እንዴት ደስ አለኝ መሰላችሁ። ነገርየው የአውሮፓውያን ባህል ነው፡፡ ወደአንድ ካፌ ቡና ለመጠጣት የገባ ገንዘብ ያለው ዓንድ ሰው ቡናውን አጣጥሞ የተጠቀመበትን ሂሳብ ሲከፍል ትርፍ ክፍያ ይፈፅማል። ማለትም አንድ ቡና ይጠጣና የሁለት ቡና የከፍላል የህንን የሚያደርገው ማንም ገንዘብ የሌለው ነገር ግን ቡና መጠጣት የፈለገ ሰው እንዲጠጣበት ነው። ሲከፍል የሚሰጠው ማረጋገጫ የለም። እርሱም አይጠይቅም። ሁሉም ነገር በእምነት ይከናወናል። ይህንን ሰስፔንድድ ኮፊ የተባለ አገልግሎት ለመጠቀም የፈለገ ሰውም "ዛሬ ሰስፔንድድ ኮፊየከፈለ አለ?" ብሎ በመጠየቅ መኖሩ ከተነገረው ከማያውቀው ሰው የተጋበዘውን ቡና ጠጥቆ አመስግኖ ይወጣል። አሪፍ አይደለች እነ ክሬዚዴይን እና አፕሪል ዘፉልን ከመኮረጅ እንደዚህ አይነቱን መኮረጅ በምድርም በሰማይም አይበጀንም ትላላችሁ? እስኪ እንወያይበት