Thursday, July 18, 2013

ክር ባጭር

በድሮ ጊዜ ነው። በሀገር ወግ በህግና በስርዓትያሳደጓትን ልጃቸውን ላግባ ባይ ጠያቂ የበዛባቸው አባወራ ማንን ከማን ለይተው ለማን እነደሚድሯት ግራ ቢገባቸው ፈተና አዘጋጁ

ፈተናው ጋቢ መስፋት ነው። አስፈላጊው መሳሪያ ሁሉ ተሟልቷል። ጋቢ፣ ክር. መርፌ ሁሉም ቀርቧል።

ያፈቀራትን ሴት በእጁ ለማስገባት የጓጓው የአዳም ዘር ውድድሩን ጀመረ። ሁሉም ጥድፊያ ላይ ነው። ማንም ማንንም አያይም። አባት እና ልጅ ብቻ ሁኔታውን ያታዘባሉ።

Thursday, May 2, 2013

ምኞት



እንደ ጎጆዬ ድባብ
                 እንደከባቢው አንድምታ
እንረታሰረች ምላሴ
                  እንዳለሁበት ሁኔታ
ዙርያዬን አቅፎ እንደያዘኝ
                 እንደሚስተዋል እይታ
ቀን ይናፍቀኛል
ማየት ያሰኘኛል 
ውስጥ የማያጮህበት
                ዝም ያለ ዝምታ።

ለካ…



ከመነጨበት የጨው ባህር ይከተታል ተመልሶ
እንባም ለካስ ይዋጣል ያታመቃል ለካስ ለቅሶ

Monday, April 29, 2013

ሰስፔንድድ ኮፊ



"ሰስፔንድድ ኮፊ" ስለሚባል ነገር ሰምቼ እንዴት ደስ አለኝ መሰላችሁ። ነገርየው የአውሮፓውያን ባህል ነው፡፡ ወደአንድ ካፌ ቡና ለመጠጣት የገባ ገንዘብ ያለው ዓንድ ሰው ቡናውን አጣጥሞ የተጠቀመበትን ሂሳብ ሲከፍል ትርፍ ክፍያ ይፈፅማል። ማለትም አንድ ቡና ይጠጣና የሁለት ቡና የከፍላል የህንን የሚያደርገው ማንም ገንዘብ የሌለው ነገር ግን ቡና መጠጣት የፈለገ ሰው እንዲጠጣበት ነው። ሲከፍል የሚሰጠው ማረጋገጫ የለም። እርሱም አይጠይቅም። ሁሉም ነገር በእምነት ይከናወናል። ይህንን ሰስፔንድድ ኮፊ የተባለ አገልግሎት ለመጠቀም የፈለገ ሰውም "ዛሬ ሰስፔንድድ ኮፊየከፈለ አለ?" ብሎ በመጠየቅ መኖሩ ከተነገረው ከማያውቀው ሰው የተጋበዘውን ቡና ጠጥቆ አመስግኖ ይወጣል። አሪፍ አይደለች እነ ክሬዚዴይን እና አፕሪል ዘፉልን ከመኮረጅ እንደዚህ አይነቱን መኮረጅ በምድርም በሰማይም አይበጀንም ትላላችሁ? እስኪ እንወያይበት