Saturday, March 10, 2018

የጥያቄዎቹ የአመላለስ መንገድ ይታረም!


በአንድ ወቅት ማህተመ ጋንዲ ‹‹የሐሳብ መለያየት ጠላትነት አይደለም፡፡ እንደዚያ ቢሆን ኖሮ ዋነኛ ጠላቴ ሚስቴ ትሆን ነበር፡፡›› በማለት ተናግረዋል፡፡ በሐሳብ መለያየት አለመዋደድ አይደለም፡፡ በአንድ ርእሰ ጉዳይ የተለያየ አቋም መያዝ የጠላትነት ምልክት አይደለም፡፡ አንዱ የስልጣኔ መለኪያ የማይጥምህን ሐሳብ ታግሶ ማድመጥ መቻል ነው፡፡
 
ያለፉትን ዓመታት የሐገራችንን ክራሞት ስንታዘብ የሥህተቱ መጀመሪያ ልዩነትን መጥላት ነው፡፡ ተቃውሞን አለመሻት ነው፡፡ በዓለም ዙሪያ የሥልጣን መንበሩ ላይ በንግስና ካሉት መኻል መቶ በመቶ ህዝቡን ያስደሰተ መንግስት የለም፡፡ አልነበረም፡፡ ወደፊትም አይኖርም፡፡ ሥርአቱን የማይደግፍ ሊኖር ይችላል፡፡ እንኳን መጥፎ የሚባለውን ድርጊት ጥሩ ነገሮችም የማይዋጡለት ሊኖር ይችላል፡፡ ነገር ግን የአጠቃላይ ስዕሉ አንድ ቀለም ነውና አይጣልም፡፡ የግዙፉ ምስል ትንሽ ክፍል ነውና ከጨዋታ ሜዳው አይባረርም፡፡

የኢትዮጵያዊያን የዘር ግንድ ምርመራና ውጤቱ


የዘር ሐረግ ምርመራ /DNA/ የሚታወሰን የቤተሰብ ዝምድናን ለማረጋገጥ ሲከወን ነው፡፡ የአባት እና ልጅነት ክርክሮችን ለመፍታት ሁነኛ መላ አድርገነው ሰንብተናል፡፡ የዘር ሐረግ ምርመራ በአብላጫ ተመራማሪዎች ይሁንታን ተችሮታል፡፡ በበርካታ ሐገሮችም ተቀባይነት አግኝቶ እየተሰራበት ይገኛል፡፡ በአሜሪካ የዜግነት እና የወላጆች መረጃ 99.99 በመቶ ተቀባይነት አለው፡፡ (100% ላለማለት ይመስላል)
ዲ.ኤን.ኤ ምንድነው?
ዲ.ኤን.ኤ (Deoxyribonucleic Acid) በጣም ጥልቅሞልዩኪል” ሆኖ ህይወት ያላቸውን ማናቸውንም ፍጡራን፣ አትክልት እንስሳትባክቴሪያ ወዘተ የዘር-ቀመር (Genetic code) ያዘለ ነው። የአንድ ፍጡር .ኤን. በዚያ ፍጡር ማናቸውም ህዋስ (ሴል) ውስጥ ይገኛል። እያንዳንዱ በምድር ላይ ያለ ፍጡር የራሱ የሆነ ልዩ ባህርይ እንዲኖረውም ያደርጋል። ይህ የሚሆነው ማንኛውም ፍጡር አካሉን የሚገነባባቸው “የፕሮቲን ሞለኪሎችን” አመራረት የሚመራው ዲ.ኤን.ኤ በመሆኑ ነው፡፡
የአንድ ህዋስፕሮቲን” የዚያን ህዋስ ተግባር ይወስናል። .ኤን.ኤ ከወላጅ ወደ ልጅ ይተላለፋል፡፡ ስለሆነም ወላጆችና ልጆች ተቀራራቢ ባህርይ እና መልክ እንዲኖራቸው ያደርጋል። አንድ ዓይነት የማይሆኑበት ምክንያት ልጆች ከሁለቱ ወላጆች ድብልቅ ዲ.ኤን. ስለሚወርሱ ነው።

የአእምሮ ንብረት እና ተዛማጅ መብቶች



ሐገራችን አባል ካልሆነችባቸው (ካልፈረመቻቸው)፣ ዓለምአቀፍ አስገዳጅ ስምምነቶች አንዱ የቅጂና ተዛማጅ መብት ነው፡፡ ይህም ለዜጎች ከሚሰጠው ጥቅም በላይ፣ ጉዳቱ የሚያመዝን በመሆኑ የተደረገ ነው፡፡ እየተጠቀምንበት ባለው ኮምፒውተር ላይ ያሉት እያንዳንዳቸው ‹ሶፍትዌሮች›፤ የእጅ ተንቀወሳቃሽ ስልካችን ላይ የሚገኙት እያንዳንዳቸው መተግበሪያዎች ‹አፕሊኬሽኖች›፤ በቅናሽ የዋጋ ተመን እጆቻችን የገቡት በዚያ ምክንያት ነው፡፡ በየኮሌጅና ዩኒቨርሲቲዎች በቅጂ (በኮፒ) እየተባዙ ተጠርዘው የተማርንባቸው መጻሕፍት፣ ከዋናው መሸጫቸው ባነሰ ዋጋ የምንገዛቸው በዚያ ሰበብ ነው፡፡ 

ስህተት በስህተት አይታረምም!


ሐገራችን ያለችበት ሁኔታ አሳሳቢ ነው፡፡ ቀድመን በትንሽ በትንሹ እያጠራቀምን ያመጣናቸው ችግሮች ተራራ አክለው ተጋፍጠውናል፡፡ ሁላችንም የየድርሻችንን በቀላሉ ያዋጣንበት የስህተት ማጥ በቀላሉ ልንቋቋመው እንዳንችል ሆኗል፡፡ ዓለማቀፍ ሚድያዎች ሳይቀሩ መስቀለኛ መንገድ ላይ መቆማችንን እየዘገቡ ይገኛሉ፡፡ ሁኔታችንን ታዝቦ፤ ድርጊታችንን ተመልክቶ፤ ነጋችንን ተንብዮ፤ አለመፍራት አይቻልም፡፡