በአንዱ የገጠር ቀበሌ ነው። ጥቂት ጎረምሶች የዓንድ
ሀብታም ገበሬን በግ በመስረቅ አርደው ይበሉና የበሉበትን ሰው በቅኔ ለመዝለፍ በማሰብ ያዘኑ መበምሰል እንዲህ ይሉታል።
እርስዎም ሳይነግሩን እኛም ሳንፈልግ
አሁን የት ይገኛል እንደርስዎ በግ
በግ መባሉን በሚገባ የተረዳውና ስራቸውንም ያወቀው፤
በጉ ተሰርቆ የተበላበት ግለሰብም እንዲህ ሲል መለሰ።
ቆየ ሰነበተ ከጠፋብኝ በጉ
እስቲ እየጋጣችሁ እናንተም ፈልጉ
No comments:
Post a Comment