Saturday, April 27, 2013

ምቀኛ ፊደል


ግጥሞችን ስትሰሙ (ስታነቡ) ወይኔ ይቺ ቃል (ይቺ ፊደል) ባትኖር ብላችሁ ታቃላችሁ? እስኪ በሱ ዙሪያ የምታጠነጥን ቀልድ ላካፍላችሁ "ምቀኛ ፊደል ነው ርዕስዋ" የፑሽኪኑ የስነ-ጽሁፍ ምሽት ገናና በነበረበት ዘመን ነበር የሰማሁዋት፡፡ ማን እንዳላት አላስታውስም፡፡

ገጣሚው ግጥም ይጽፍና ቤት አልመታ ይለዋል እናም ችሎታውን ሳይሆን ፊደላትን ይረግማል ምቀኛ እያለ

እነሆ አንዱ ግጥም


ልቤ ባንቺ ፍቅር እጅጉን ዋተተ
እባክሽ ፍቅሬ ሆይ ነይና እንተ

ይልና ከስር "" ምቀኛ ፊደል! ብሎ ይፅፋል፡፡ ግጥሙ ግጥም እንዳይሆን ያደረገች፡፡

አንድ እንጨምር
ከቶ እንደልጅነት ምን ጥሩ አለና
አልጋላይ ቁጭ ብሎ ዝም ብሎ መዝናና

"
" ምቀኛ ፊደል

No comments:

Post a Comment