ከዳዊት ዓርአያ
/አጭር ልቦለድ /
ብርሀን ባለበት የጨለማ ግርማ ይገፈፋል። ጨለማ ሲኖርም የብርሀን ጸጋ ስፍራውን ያስረክባል። ይህ ክፍል እንደዚያ አይደለም
፡፡ ብርሃንም ጨለማም ነግሰውበታል። ሠሃራም ሳይቤሪያም፣ ወተትም ቡናም ያልሆነ ማኪያቶ ክፍል ነው።
ጡንቻውን በስፖርት ያደለበ፣ አንጎሉን በዕውቀት ያጣበበ፣ የሰውን ልጅ ከትንኝ ነፍስ የሚያስተካክል፣ ራሱን ከትቢያ በላይ የሚያበክት፣ አማኝ ከሀዲ ተጠራጣሪ… ከያይነቱ ተውጣጥቶ የተጠራቀመ የ’ሰው’ ዓይነት አለበት።
ከጥፋታቸው እንዲማሩ ወይንም በወንጀላቸው እንዲማረሩ የሚታሸጉት ይህ ስፍራ ከአንስታይ ፆታ በቀር የእድሜ ገደብ የለበትም። የትምህርት፣ የኑሮ፣ የዕውቀት፣ የእምነት፣ የአስተሳሰብ ልዩነት ቢኖርም ኗሪዎችን ከመግባባት አያግድም። ባለመግባባት ከሚፈጠር ግጭት በላይ በመመሳሰል የሚፈጠረውን ’ሰላም’ ሁሉም ተገንዝቧል። መስሎ አስመስሎ ቀን ይገፋል። በተመሳሳይ ወግ ተመስጦ ተመሳሳይ ሳቅ ይስቃል።
የወንድወሰን ይህንን ሰራዊት የተቀላቀለው በቅርቡ በመሆኑ በነባር አባላት ጀርባቸው ካልተጠና ግለሰቦች መሀከል ከቀደንቶቹ ተራ ይሰለፋል። የዋስ መብት የተከለከለ ወይም ዋስ የሌለው ወይም ዋስ ያልፈለገ ሰው የፍርድ ሂደቱን በሚከታተልበት በዚህ ክፍል ከሚዘወተሩ ድርጊቶች ዋነኛው አዲስ ገቢን ማፋጠጥ ነው። “ሌሎች ሊያደር ጉብህ የማትፈልገውን …” “ነግ በኔ” ይሉት ፈሊጥ እዚህ አይሰራም። በነባሮች አለቃ አማላይነት አሳፋሪም አስነዋሪም ምስጢር በግድም በፈቃድም ይዘከዘካል። ታዳሚው በሚበልጠው አረመኔ እየተደመመ ምናልባትም በጥሩ እውቀትና ብቃት የውንብድና ተግባሩን ለማከናወን የተሻለ ቴክኒክ ባለቤት ሆኖ ለመውጣት እንዲችል ኮርስ ይወስዳል። ይሰጣል።
“ወንዴ!... አንቺ? ለመሆኑ በምንድነው ሸቤ የገባሽው?”
‘አንቺ’ የሚለውን መጠሪያ አይወደውም። በምንም አይነት ክስተት በየትኛውም
አጋጣሚ ‘አንቺ’ ሲባል ያመዋል፡፡ አሁን ህመሙን ውጦ አመለካከቱን ደብቆ ለመመለስ ተሰናዳ።አቋሙ ወንዳወንድነትን የተላበሰ ቢሆንም
ድምፁ፣ አኳኃኑ እና እንቅስቃሴያዊ ሁኔታው ተቃራኒ ፆታውን ያስመስሉታል፡፡
“የተያዝኩት በቺክ ነው….” አፋቸውን ከፍተው እያደመጡት ነው። እስከዛሬ ባለው ህይወቱ ተረት ከሚያወራላቸው ህጻናትና
ከወላጅ እናቱ በቀር በትኩረት ነገሬ ብሎ አድምጦት የሚያውቅን ሰው አያስታውስም።ደስታ ጎበኘው እየፈነደቀ ትረካውን ቀጠለ።
ከታዳሚዎቹ መሀከል አንዱ “ማለት… እንዴት?” ሲል በጥርጣሬ ጠየቀው።
ወንደሰን በጠባብዋ እስርቤት ውስጥ ልዩ ነው። ከነበሩት ያላበረ ገፅ አለው። ከመንጋዋ በመለየት ከፍ ከፍ ያለች ማሽላ
የወፍ እራት እንደምትሆን ሁሉ ዘግይታ የበቀለችዋም ከመረገጥ አታመልጥምና በዝያች ልዩ መሆን በማይታወቅባት ክፍል- የመለያየተትን
ተፈጥሮ በመቀበል በመቻቻል ሳይሆን በማፈን በሚገለጥባት ጠባብ ክፍል መመሳሰሰል ባለመቻሉ ትኩረት ሳበ።
“እ… አባባሌ… ደፍረሀል ተብዬ።”
ሁሉም ደነገጡ። ድንጋጤአቸው ተጋባበት። በርካታ ሰቅጣጭ ወንጀሎች እጅግ መሪር ተግባሮች ሲነገሩ እንደዘበት በሚታለፍበት ቤት የሱ አስገድዶ መድፈር ሲያስደነግጥ ያስተዋለው ወንደሰን አንደበቱ ተሳሰረ።
“ቺኳ ፈልፈላ ነበረች…. …. ምን ሰይጣን እንዳሳሳተኝ. . .” በተጋጠሙ ጥርሶቹ መሀል ለንቦጩን ደፈጠጠ። ዓይኖቹ ውሀ ተሸከሙ። “አሁን ላይ ሆኜ ሳስበው . . . ” ንግግሩ ከዚህ በላይ እንዳይቀጥል ሳግ ጉሮሮውን ደፍኖ አቋረጠው።
ያደመጡት ከሹፈት እስከ ሀዘኔታ፣ ከሳቅ እስከ ጥርጣሬ በርካታ ምላሾች አስተናገዱ። እናባውን ገቶ ትረካውን ጀመረ
“እ . እ . ል . ልጅቷ . . .” መቀጠል አልቻለም። በግፅ የሚያስታውቅ መደነጋገር ፍርሀትና መሸበር በተጹ ላይ መነበብ ጀምሯል። በሁኔታው ግራ የተጋቡ የማወቅ ፍላጎታቸው በከፍተኛ መጠን ናረ።
“እ . እ . ል . ልጅቷ . . .” መቀጠል አልቻለም። በግፅ የሚያስታውቅ መደነጋገር ፍርሀትና መሸበር በተጹ ላይ መነበብ ጀምሯል። በሁኔታው ግራ የተጋቡ የማወቅ ፍላጎታቸው በከፍተኛ መጠን ናረ።
“ለማምለጥ አልሞከርሽም?”
“ወዲያው ነው የተያዝኩት”
ሌላ ጥያቄ ካንዱ ጥግ ‘”ቦታው የት ነው?”
“እ . . . ቦ . ቦታው”
“እ . . . ቦ . ቦታው”
“ጭራሽ ቦታውን አታውቂውም?”
በፍጥነት “እ . . . እንትን ጓ . ጓሮ” አለ።
እርስ በርሳቸው ተያዩ። አንዳቸው ካንዳቸው ተጠቃቀሱ። ጥርሱን አፏጨ። እንደዚህ ያለውን ተግባር አይወድም። አይፈልግም። ዓይን በመፍራት ጨለማ የተወዳጀበትን ጊዜ ያስታውሰዋል። ከሰው ብቻ ሳይሆን ከራሱ የተደበቀባቸውን ዘመናት ያስታውሰዋል። ስለዚህ ያይን ንግግር አይመቸውም።
“እባካችሁ . . . እባካችሁ ተውኝ!” በተማፅኖ ቃላት ባይኑ እያማተረ ተለማመጣቸው።
“እንተውሀለን። ነገር ግን . . .! ”
“ግን ምን?”
“አንድ ነገር ይቀረናል” በመጠኑ ተረጋጋ። የያንዳንዷ ሰከንድ ቁመት ከሰዓታት በላይ አድጎበት ነበር። ከ አንድ መልስ በኋላ ሳይፈቅድ የወሰዱትን በፈቃዳቸው ይመልሱለታል። ሙሉ እፎይታውን ይረከባል።
“እሺ ምን . . .!” ጠየቃቸው።
“ሱሪህን እንድታወልቅ እንፈልጋለን”
“እ!!” ደነገጠ። በጣም ደነገጠ። እጅግ በጣም ደነገጠ። ልቡን ያዘ። እየመታች ነው። እንዲያውም ከወትሮው በፈጠነ መልኩ ትዘላለች። የግንጋሩን ሙቀት በተንከረፈፈው አይበሉባው ለካ። ያተኩሳል። “ስለዚህ አለሁ ማለት ነው?!” አለ። ለሱ ይህ ጥያቄ ሞት ብቻ አይደለም፡፡ ይህ ጥያቄ ለሱ ከህይወት በላይ ትርጉም ያለው ነው።
“አውልቅ እንጂ!!” ከግራ ከቀኝ አጣደፉት።
ካንገት በላይ የፅዳት አገልግሎት ሲያከናውኑ የቆዩ እጆቹን ወደታች አሰማራቸው ። እንደሚነድ ችቦ፣ እንደሚደፋ ቁሻሻ
ከየተሸጎጡበት ጥግ በፍጥነት ተስፈንጥረው ወደአንድ አቅጣጫ በመጠራቀም የተበታተነ አቀማመጣቸውን አስተካከሉ። ከአይናቸው ሽፋል በቀር
እንቅስቃሴ ተገታ።
እረጭ!
እረጭ!
በኤሊ ፍጥነት የፈታው የሰፊው ስስ ሱሪው የመታጠቂያ አዝራር ከጁ አፈትልኮ እጫማው ስር ለመከመር ከአይን ጥቅሻ የረዘመ ጊዜ አልወሰደበትም። ከፍ ለማለት ሲቃጣ ጋሬጣዎች ጥቂት አይደሉም። ነፋስ ጉዞን ያስተጓጉላል፤ አቅም በድካም ይፈተናል። ቁልቁል የመውረድ ተፈጥሮ ግን እንዲያ አይደለም የመሬት ስበት የራስዋን አስተዋፅኦ በማዋጣት ሂደቱን ታፋጥናለች።
አዩት። በባዶ ቃላት ብቻ በአንደበት ሽንገላ ሲተማመኑ የቆዩ ሁሉ ‘ማየት ማመን ነው’ን ተገበሩበት።
ሳያዩ ያመኑ ብጹእነታቸውን፣ ወላዋዮች እምነታቸውን አገኙ። ገሚሱ የፈጣሪውን ምስጋና በሹክሹክታ አደረሰ፤ ከፊሉ አግራሞቱን፤
ቀሪው ሀዘኔታውን፤ ሌላው ዝምታውን አመነዠከ። ልጁ የወንድነት ተፈጥሮው በቦታው ላይ የለም። ወንድም ሴትም አይደለም። የለውም።
“ለምን ዋሸሽን?”
ለአፍታ በዝምታ ህሊናውን ሰብስቦ በልበ ሙሉነት መናገር ጀመረ። መሸበሩ ለቆታል። እውነቱን በእንባ ለውሶ ተረከላቸው
“የህፃን ጩኸት ከእንቅልፌ አባነነኝ። በፍጥነት ወደስፍራው ሮጥኩ። ህጻኗ በደም ተነክራ ራስዋን ስታለች። እንደኔ ጩኸቱ
የጠራቸው ተሰበሰቡ። እጄ ላይ ተዝለፍልፋ አገኟት።
እጅ ከፍንጅ . . .” በምድር ፍርድቤት ማስረጃ የሌለው
ንጹህ ከአዳፋው እኩል ነው። ሰነድ ያወደመ ወንጀለኛ ባለ ነፃነት ነው።
“እኔ አይደለሁም ካላመናችሁ ላሳይ . . . አትያ . . . አትላቸውም ነበር?”
“ለኔ ‘ወንድ አይደለሁም!’ ብሎ ከመናገር ፆታ እንደሌለኝ ላደባባይ ከማሳወቅ ይልቅ÷ በወንድ ወንጀል ወንጀለኛ መሆን
ትልቅ ክብር ነው”
ትኩስ እንባው ጉንጩን አልፎ ወለሉ ላይ ተንጠባጠበ።
![]() |
|||||
![]() |
![]() |
||||
No comments:
Post a Comment