‹‹ፍቅር ይዞህ ያውቃል ለመሆኑ?››
‹‹አዎን››
‹‹ከማን ጋር?››
‹‹ከኢትዮጵያ››
‹‹አሃ! የፍቅረኛህ ስም ኢትዮጵያ ነበር?››
‹‹አዎን!››
‹‹ለምን ከኢትዮጵያ ጋር ተለያያችሁ?››
‹‹መንግስቱ ሃይለማርያም እና ድርጅቱ ትግላችንን እና ኢትዮጵያ ሀገራችንን ገደሏት››
‹‹ዋለልኝ! ለምን ታሾፍብኛለህ? ምንድነው የምትቀባጥረው?››

ከጭምትነቱ ወጥቶ ጣራው እስኪሰነጠቅ ድረስ ሳቀ፡፡ ቲያትር የሚሰራ ነው የሚመስለው፡፡ ለደቂቃዎች ሳቁን
አላቆመም፡፡ ሳቁ ግን የደስታ ሳይሆን የንዴት እንደነበር ያስታውቃል፡፡ አይኖቹ እና ፊቱ ቀሉ፡፡ ደምስሮቹ በአንገቱ
እና በፊት ገጹ ላይ ተገታተሩ፡፡ የመጨረሻ ጥያቄዬ በጣም እንዳበሳጨው ተረዳሁ፤
‹‹ለነገሩ ሮዛ አንቺ ምን ታደርጊ፣ አልፈርድብሽም የኔ ትውልድ ብትሆኚ ነበር ህመም እና ስቃዬ የሚገባሽ››
ከላይ የለበሰውን ብርድልብስ እና አንሶላ ሰብስቦ መሬት ላይ በሀይል ወረወራቸው፡፡ እንዳያንቀኝ ፈርቻለሁ፤ በሆዱ አልጋ ላይ እጁን ዘርግቶ ተኛ፤
‹‹ጀርባዬ ይታይሻል? የውስጥእግሬን ተመልክተሸዋል?!››
ጩኸቴን ለቀቅኩት፡፡ ጀርባው፣ ቂጡ፣ የታፋው ጀርባ ባቱ እና ውስጥ እግሩ ሰንበር በሰንበር ናቸው፡፡ አሁን የተገረፈ ያህል ምልክቶቹ በሙሉ አሉ፡፡ የተገረፈባቸው አለንጋዎች ስጋን ቦጭቀው የሚያነሱ እንደነበር ጀርባው እና ውስጥ እግሩ ላይ ካሉት ጉድጓዶች መናገር ይቻላል፡፡ ዋለልኝ አንጀቴን በላኝ፡፡
‹‹ለተሻለች ኢትዮጵያ እንቅልፍ አጥተን 24 ሰዓት ማሰባችንና በኢትዮጵያ ክፉ ፍቅር መለከፋችን ነው ለዚህ ያደረሰን፡፡››
ዋለልኝ እየሰማሁት እንደሆነ ለማረጋገጥ ፊቱን አዙሮ በአትኩሮት ተመለከተኝ፡፡ ፊቱን መልሶ ንግሩን ቀጠለ፡፡
‹‹ስለ ኢሀፓ ምንም የማያውቁትና ምንም ዓይነት ተሳትፎ ያልነበራቸው ሶስት ወንድሞቼ ደብተር ይዘው በመናፈሻ ውስጥ ሲያልፉ ለምን ተገደሉ? እህቴ ማርታ ሬሳዋ ጧት በመኖሪያ ቤታችን በር ላይ ለምን ተጣለ? የልብ ጓደኛዬ ሽፈራው ለምን ቤተሰቦቹ የጥይት ክፈሉ ተባሉ? ከነዛ ሁሉ ጓደኞቼ ሲሶዎቹ ለምን ተረሸኑ? መላኩ ተፈራ ወገኖቼን ለምን ከተራራ ገፍትሮ ገደላቸው? ለምን ወገን አልባ አደረገኝ? . . .››
ሳላውቀው እንባዬ ቁልቁል ፈሰሰ፡፡ አሁን ውል ብሎ ባይታየኝም እናቴ አምርሬ የምጠላው አባቴ የኢህአፓ ታሪክ አንድ አካል እንደሆነ በተደጋጋሚ እንዳጫወተችኝ ትዝ አለኝ፡፡ ስለዚያ ዘመን መንፈስና አጠቃላይ ሁኔታ ያሳወቅኝ ያነበብኳቸው የክፍሉ ታደሰ ‹‹ያ ትውልድ›› ደራሲውን የማላስታውሰው ‹‹የትውልድ እልቂት›› የሚባሉ መጻኅፍት ናቸው፡፡
‹‹ተራ ፍቅር አልነበረም ከኢትዮጵያ ጋረ ያሳለፍኩት፣ ገዳይ ፍቅር ነበር፡፡ ስለ አንድ ኢትዮጵያ፣ ስለ ነጻነት፣ ስለ ፍትሕ፣ ስለ እኩልነት በየደቂቃው እንደ ወፈፌ የሚያስለፈልፍ ፍቅር ነበር፡፡ ያለማቋረጥ በየቀኑ ለ ሁለት ወራት ያህል ጾም ጸሎት በማይቀረውና ሰንበትን በቤተክርስቲያን በሚያሳልፍ የደርግ ሎሌ ተገርፌአለሁ፡፡ ከዓመታት እስር በኋላ እንደጠላት ካየችኝ ኢትዮጵያ ተሰደድኩ፡፡ እንግሊዝ ከገባሁ በኋላ በተከተሉት ዓመታት ቅዠት ያስቸግረኝ ነበር፡፡ ሴት ታውፎ ለመተኛት የበቃሁት እዚሁ እንግሊዝ ውስጥ ረዥም ጊዜ የፈጀ የስነልቦና ህክምና ካደረኩ በኋላ ነው፡፡ ወሲብ መፈጸም ግን አልችልም ስለ ኢትዮጵያ ስል ተኮላሽቻለሁ፡፡››
/ሮዛ- ከተባለው መጽሀፍ የተቆነጠረ/

No comments:
Post a Comment