እንደ ዕድል ሆኖ ዛሬ ከማይክራፎኑ ጅርባ ነህ፡፡ እንዳጋጣሚ ሆኖ ብዕርህ የብዙዎችን አትኩሮት ስቧል፡፡ወደውም ሳይወዱም
ይሰሙሀል፡፡ ምርጫ ያጣም አማራጭ የፈለገም ያነብሀል፡፡
እዚህ ጋር ቆም ብለህ አስብ . . .
ይህ ውድ መዓድ፣ በርካቶች ፈልገው ያጡት፤ በርካቶች ከኔ የተሻለ ይጠቀምበት ብለውበትህትና ያለፉት መድረክ የተከበረ
ነው፡፡ ዛሬ ዛሬ ነገር ተበላሽቶ ማንም ፈነጨበት እንጂ . . .
እና ምን ይጠበስ? አይዞህ ምንም አይጠበስም፡፡
እድሉን ማግኘትህን በሚገባ ተገንዘብ፡፡ አዎ! ቀጥለህ ደግሞ ራስህን ለቦታው ብቁ ለማድረግ ትጋ፡፡ ቀጥሎ . . . ከታላላቆችህ
ብቻ ሳይሆን፣ ከእኩችህ ብቻ ሳይሆን፣ ከታናናሾችህ ለመማር ዘወትር ዝግጁ ሁን፡፡
ደግሞ አንብብ . . . የተፃፈውን ብቻ ሳይሆን በመስመሩ
መሀል ያለውን ስውር ሀሳብ አንብብ፡፡ አካባቢህን አንብብ፡፡ ራስህን አንብብ፡፡ ዙሪያ ገባውን ሁሉ አንብብ፡፡
እነዚህን ሁሉ ስላደረግህ
ምሉእነት የመጣ መሰለህ አይደል? አልመጣም፡፡
አይመጣምም፡፡ ሙሉ ነኝ ያለ ጉድለቱን ይረሳል፡፡ ያልጎደለ አይሞላም፡፡ የሞላ ያፈሳል/ያባክናል/
ስለዚህ ቋትህ ሁልጊዜ ሰፊ ምናብህ ዘወትር ምጡቅ ይሁን፡፡
በመጨረሻም
አሁን ተናገር፡፡ አሁን ጻፍ፡፡ አሁን ደግፍ፡፡ አሁን ተቃወም፡፡ ሚዛን ትደፋለህ! ውሀ የቋጠረ ሐሳብ አለህ!
ራዲዮኑ ሲጠፋ፣ ቲቪው ሲዘጋ፣ ጋዜጣው መጽሄቱ ታጥፎ የሚብሰለሰል አንዳች ቁምነገር ይኖርሀል፡፡ በርታልኝ ወዳጄ!!!
No comments:
Post a Comment