ክቡር ጦማሪ ሆይ፡- መቼም በሆነ የታሪክ አጋጣሚ ዘመኑ በፈቀደልን ስሜትን የመግለጫ፣ ሀሳብን የማስተላለፊያ መንገዶች በመጠቀም የልባችንን መተንፈስ ከጀመርን ሰነባበተ እነሆ እኔም ሳይገባኝ ወደላይ ተንጠራርቼ ምክር ለመለገስ ዳዳኝ። አንተም እንደምታውቀው ባለፈው ጊዜም ፓስት አድርገህ እንዳየሁት <<ሰዎች ለሰዎች ያለስስት የሚለግሱት ነገር ምክር ነው!>> እናም ታናሽነቴን ሳታይ የምለውን እንደምትቀበለኝ ተስፋ አደርጋለሁ።
1ኛ- የህዝቡን የልብ ትርታ አዳምጥ፡-
ሰሞነኛ ትኩሳቶችን እየተከታተልክ የሚመስልህን ነገር በፍጥነት እና በተከታታይ በገፅህ ላይ ማስፈር ተገቢ ነው። ነገርየው
የምታምንበት ባይሆንም እንኳን አጋጣሚው በርካታ 'ላይኮች'ን ሊያስገኝልህ ስለሚችል ተመሳሳይ ገጠመኞችን በቀላሉ ማለፍ አይገባም። የፖለቲካም
ሆነ የሀይማኖት፤ የሀገር ውስጥም ሆነ የውጭ ፤የኪነጥበብም ሆነ የእስፖርት፤ የግለሰብም ሆነ የድርጅት፤ የቡድንም ይሁን የተቋም ሰሞነኛ ወሬዎችን አትለፍ። ፍላጎት የለኝም፣ ስለጉዳዩ
የማውቀው ነገር የለም፣ በቂ መረጃ አልሰበሰብኩም ወዘተ … የሚሉ ተልካሻ ምክንያቶችን አስወግድ ብታውቅም ባታውቅም ቢጥምህም ባይጥምህም
ብታምንበትም ባታምንበትም ፃፍ።
2ኛ ደፋር ሁን፡-
ማንም ሰው እሱ ለማለት የሚፈራውን ወይም የሚያፍረውን ነገር ፍርሀቱን ደብቆና ሀፍረቱን ተጋፍጦ የሚልለት ሰው ሲያገኝ ጀግና ብሎ ያሞካሸዋል። ምርጥ ብሎ ይዘምርለታል።
አንተም ያንኑ አድርግ። ወሲባዊ ነጥቦች ሲነሱ ውስጥህን አጀግነህ በባህል ማነቆ የተጠፈረው ማህበረሰብ የማያወጣቸውን ቃላት እየጠራህ፤
የማይደፍራቸውን ሀሳቦች እያነሳህ ፃፍ። ያኔ ላይክና ኮሜንት ይጎርፍልሀል። ፖለቲካዊ ነጥቦች ሲነሱም አይረባም፣ ይውደም፣ ሌባ፣ ሙሰኛ፣ዘረኛ የመሳሰሉ ቃላትን ተጠቅመህ በመሳደብ
‘ኧረ እንዳትታሰር’ ‘አንተ ልጅ እንዳያስገቡህ ብቻ’ የሚሉ ኮሜንቶችን ከሰበሰብክ እቅድህ ግቡን መቷል ማለት ነው። የዘርና የሀይማኖት
ጉዳዮችንም ድፈር። ገዢውን ፓርቲ ብትደግፍም ባትደግፍም መፃፍ ያለብህ ተቃውሞ ብቻ ነው። ግለሰብንም ተቋምንም እንዳትምር ያለርህራሄ ተቃወም። የምትቃወመውንም ፃፍ።
3ኛ-ጭንወትን አስወግድ፡-
ብዙ ምርጥ ጦማሪዎች ሰፊ ታዋቂነትን እና ተወዳጅነትን ሳያገኙ በጥቂት የሚያውቋቸው ሰዎች አድናቆት ብቻ ተወስነው ሊቀሩ
የቻሉት ይህንን ምስጢር ባለመረዳታቸው ነው። አንድ ሀሳብ አንስተህ ለመፃፍ ወይም አንድ ግለሰብ ጠቅሰህ ለመዝለፍ ስትሰናዳ
<<ከዚህ በፊት የኔን ሀሳብ ከኔ በተሻለ መንገድ ያለው ሰው ይኖር ይሆን?>> <<ጽሁፌ ከስሜት የጸዳ እና በእውቀት የተመሰረተ ነውን?>>
ብለህ አትጨናነቅ፤ መፃህፍት አገላብጠህ፣ ድህረገፆች አስሰህ አዋቂዎች ጠይቀህ . . . ለሚሉ የጊዜ ቀበኞች ጆሮ አትስጥ - የመጽኀፉን መግቢያ ወይም የተሰጡ አስተያየቶችን ገረፍ ገረፍ ካደረክ ከበቂ በላይ ነው። ምክንያቱም ጊዜ የለህም መፃፍ አለብህ። <<ሀሳቡ ለአቅመ ስነፅሁፍ ደርሶ ይሆን? ወይስ ከመደጋገሙ ብዛት የነተበ ነው>> አትበል። መብራት የጠፋ ለት
መብራት ጠፋብን
ጨለማ ዋጠን
እስኪ ምን የበጀን
አምላክ መላ በለን እያልክ አዚም። <<ይህንን በማለቴ የምጨምረው ወይም የማጠፋው እሴት ይኖራል?>> ብለህ ብዙ ልትጦምር የምትችልበትን ጊዜ አታባክን ተመሳሳይ ሀሳቦች በማንሳት 5ሺ ላይክ ባጭር ጊዜ አይገኝም።
መብራት ጠፋብን
ጨለማ ዋጠን
እስኪ ምን የበጀን
አምላክ መላ በለን እያልክ አዚም። <<ይህንን በማለቴ የምጨምረው ወይም የማጠፋው እሴት ይኖራል?>> ብለህ ብዙ ልትጦምር የምትችልበትን ጊዜ አታባክን ተመሳሳይ ሀሳቦች በማንሳት 5ሺ ላይክ ባጭር ጊዜ አይገኝም።
4ኛ - qwertyuiop[]asdfghjkl;’zxcvbnm,./qwertnbvsdfghjcxczadopsdfghjodwwoxnmoe9=-a
5ኛ- nbvsdfghjcxczadopsdfghjodwwoxnmoe9=-a zadopsdfghjozadopsdfghjozadopsdfghjo
- የምጽፈው አንድም፡- ሀሳቤን የሚጋራኝ ፍለጋ (የማውቀውን ለማጋራት)፤ አንድም፡- ከኔ በተቃራኒ የሚያስብ ካለ ምልከታውን በመሻት፤ አንድም፡- አወዛጋቢ ርዕሰ ጉዳይ ሲሆን የጠራ አመለካከት ለመያዝ፤ ይህ ካልሆነ ደግሞ በሆነ የዓለም ጥግ እንደዚህ የሚያስብ አንድ ሰው መኖሩን ለማሳወቅ ነው። ብለህ የምታስብ ከሆነ 5ቱን ነጥቦች መተግበር አይጠበቅብህም። ማሳሰቢያ፡-ተራ ቁጥር 4 እና ተራ ቁጥር 5 አልነበብ ካልዎት የራስዎን ሀሳብ ያስፍሩበት
hahahah yamral antem mokerew kesera
ReplyDelete