‹ሱዛን ፎርማን› የተባሉ ጸሐፊ ‹‹The Media of Advertising›› በተሰኘው መጽሐፋቸው ስለ ማስታወቂያ አጀማመር
ሲገልጹ
‹‹ማስታወቂያ ስረ መሰረቱ በጥንታዊት ሮም መኳንንቶችን ለማስደሰት የሚደረጉ ድብድቦች /Gladiators/ በታላላቅ
አደባባዮች የሚካሄዱ መሆኑን የሚያስተዋውቁ፤ በመካከለኛው ዘመን የሞት ፍርድ በአደባባይ የሚፈፀም መሆኑን የሚያመላክቱ፤ በአሜሪካ
ጠረፍ በትልቁ ተፅፈው የሚንጠለጠሉ
የ ’ወንጀለኛ ይፈለጋል’ ማሳሰቢያዎች ናቸው፡፡›› ይላሉ፡፡
በግብጽ በ 3200 ዓ.ዓ አካባቢ በተሰሩ የማምለኪያ ህንፃዎች ላይ ማንኛው ንጉስ እንዳስገነባው የሚጠቁሙት ጽሁፎች ከማስታወቂያ
ይመደባሉ የሚሉ ምሁራንም አሉ፡፡
በታሪክ የመጀመሪያው ተብሎ በ (Encyclopedia Britanica,Vol 1 ,180) የተመዘገበው የጽሁፍ ማስታወቂያ
‹‹ሼም የተባለው ባሪያ ሃፑ ከተሰኘው
አሳዳሪ ተሰውሯል፡፡ ሃፑ የቴቢስ መልካም ዜጎች ሁሉ ይህን የጠፋ ባሪያ ቢመልሱለት ይወዳል፡፡ ባሪያው ባለቡናማ ዓይን ነው፡፡ ያለበትን
አካባቢ ዜና ላመጣ ግማሽ የወርቅ ሳንቲም ይሰጠዋል፡፡ ሼምን ወደአሳዳሪው ለሚመልስ ደግሞ እንደፍላጎቱ ልብስ የሚደሸመንለት ሲሆን
ሙሉ የወርቅ ሳንቲምም ይሰጠዋል፡፡››
የሚል ሲሆን ከ 3ሺህ ዓመት በፊት በፓፒረስ ላይ የተጻፈ መሆኑ ተገልጧዋል፡፡
በዘመናዊና በተደራጀ መልኩ ከቀረቡት ማስታወቂያዎች በፊት ግን ሰዎች ድምጻቸውን ከፍ በማድረግ ማስታወቂያቸውን ይናገራሉ፡፡
በሐገራችንም ይህ ተግባር የተለመደ ነበር