መግቢያ
ጥቂት የማይባሉ አያሌ ዘመናትን ወደፊት ተሻግረን ከቀናቶች መካከል ባለች የተለመደች አዘቦት ቀን ላይ ነን፡፡ ተንጠራርተን እያስተዋልናት ባለችው በዚህች ተራ ቀን ድሮ ምን ይመስል እንደነበር ልንቃኝ ነው፡፡ በአሁን የጊዜ ፈረስ ተፈናጠን ነገን በዛሬ ልናነፃፅር . . .
ትዝታ አይደለም፡፡ ትዝታ የኖሩትን በምናብ መድገም ነው፡፡ ከትውስታ ጓዳም ከህልውና መድረክም ሊሰርዙት አይቻልም፡፡ መከሰቱም ማለፉም የተረጋገጠ ነው፡፡
ትንቢት አይደለም፡፡ ትንቢት ያልኖሩትን መገመት ነው፡፡ ስምረቱንም ክሽፈቱንም ማረጋገጥ ከባድ ነው፡፡
ይህ ከሁለቱም ይለያል፡፡ ሁለቱንም መሳይ ገፅ አለው፡፡