ክቡር ጦማሪ ሆይ፡- መቼም በሆነ የታሪክ አጋጣሚ ዘመኑ በፈቀደልን ስሜትን የመግለጫ፣ ሀሳብን የማስተላለፊያ መንገዶች በመጠቀም የልባችንን መተንፈስ ከጀመርን ሰነባበተ እነሆ እኔም ሳይገባኝ ወደላይ ተንጠራርቼ ምክር ለመለገስ ዳዳኝ። አንተም እንደምታውቀው ባለፈው ጊዜም ፓስት አድርገህ እንዳየሁት <<ሰዎች ለሰዎች ያለስስት የሚለግሱት ነገር ምክር ነው!>> እናም ታናሽነቴን ሳታይ የምለውን እንደምትቀበለኝ ተስፋ አደርጋለሁ።
1ኛ- የህዝቡን የልብ ትርታ አዳምጥ፡-
ሰሞነኛ ትኩሳቶችን እየተከታተልክ የሚመስልህን ነገር በፍጥነት እና በተከታታይ በገፅህ ላይ ማስፈር ተገቢ ነው። ነገርየው
የምታምንበት ባይሆንም እንኳን አጋጣሚው በርካታ 'ላይኮች'ን ሊያስገኝልህ ስለሚችል ተመሳሳይ ገጠመኞችን በቀላሉ ማለፍ አይገባም። የፖለቲካም
ሆነ የሀይማኖት፤ የሀገር ውስጥም ሆነ የውጭ ፤የኪነጥበብም ሆነ የእስፖርት፤ የግለሰብም ሆነ የድርጅት፤ የቡድንም ይሁን የተቋም ሰሞነኛ ወሬዎችን አትለፍ። ፍላጎት የለኝም፣ ስለጉዳዩ
የማውቀው ነገር የለም፣ በቂ መረጃ አልሰበሰብኩም ወዘተ … የሚሉ ተልካሻ ምክንያቶችን አስወግድ ብታውቅም ባታውቅም ቢጥምህም ባይጥምህም
ብታምንበትም ባታምንበትም ፃፍ።
2ኛ ደፋር ሁን፡-